Show cover of Sovereignty Sources

Sovereignty Sources

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

Tracks

ሩሲያዊው ታላቁ የስነ ፅሁፍ ሰው፣ አሌክሳንደር ፑሽኪን ጥንተ ኢትዮጵያዊ ሥር መሠረት እንዳለው ያውቃሉ? ከሚያስቡት በላይ ሁለቱን ሀገራት ያጋመደ ታሪክ ነው!  የቀደመ ታሪኩ ከወንድ ቅመ አያቱ እናት አብራም ፔትሮቪች ጋኒባል ይመዘዛል — ከባርነት እስከ ነፃነት የተሻገረ የኢትዮጵያዊ ልዑል አንፀባራቂ ታሪክ. 💫  የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስ መሰናዷችንን  የሩሲያ ቋንቋ ቀን እና የአሌክሳንደር ፑሽኪንን ልደት ምክንያት አድርግ ኢትዮጵያዊው ጸሐፈ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ  እንግዳ አድርገናል።“ያለፈበት ስርዓት ከኢትዮጵያ ጋር ያስተሳስረዋል። በርካታ ነገሮች ፑሽኪንን ከኢትዮጵያ ጋር ያስተሳስራሉ።”  ሲሉ ጸሐፈ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ እና የፑሽኪን አሻራ መካከል ስላሉ ያልተነገሩ ትስስሮችን ያግኙ

6/6/25 • 60:00

የሶቨርኒቲ ሶርስ የዕለቱ ዝግጅት ትኩረቱን በሳይበር ደህነነትን ላይ ሲያደርግ ፣ የአፍሪካ ሀገራት ለዜጎቻቸው የሚሰጧቸዉን  ዲጂታል አግልግሎቶችና  የተደቀነባቸውን የሳይበር ጥቃቶች በስፋት ይዳስሳል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ የሶፍትዌር ኢንጅነር እና የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት አበልፃጊ /ዴቨሎፐር/  አቤል በነበሩን  ጋብዘናል፡፡በአፍሪካ እያደገ የመጣው ዲጂታላይዝ የሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ምክንያት በማድረግ የአፍሪካ ሀገራት የሳይበር ደህንነትን በተመለከተ ንቁ የሆነ አካሄድ መከተል ይገባቸዋል፡፡““ለምሳሌ አሁን ላይ የምንጠቀመው የመረጃ ማዕከል ሊሆን ይችላል፣ ኔትዎርክ ኢንተርኔት ኤክስቼንጅ ፖይንቶቻችንም ሊሆኑ ይችላሉ እንዳሉ ከምዕራባውያን ጋር የተገናኙ ነገሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ለእነዚህ ነገሮች መፍትሄ መስጠት፣ ለምሳሌ አፍሪካውያን እንደ አፍሪካ ተቀናጅተው አንድ ኢንተርኔት ኤክስቼንጅ ፖይንት እንዲኖራቸው ሁለተኛ የራሳቸው የመረጃ ማዕከል ቢኖራቸው  መረጃ የመውጣቱ ዕድል ይቀንሳል፡፡" ሲል ከፍተኛ የሶፍትዌር ኢንጂነር እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት አበልፃጊ ወይም ' ዲቨሎፐር' አቤል በነበሩ ተናግሯል ። ይህም  ከፖርታል ሳይበር ጥቃት  ሚስጥራዊ  መረጃን ፣ ዲጂታል መሠረተ ልማትን እና አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶችን  መጠበቅ ላይ ሚናው ወሳኝ ነው ፣ ለዚህ ደግሞ ዲጂታል ሉዓላዊነት ሊሰመርበት ይገባል፡፡‘‘ ዲጂታል ሉዓላዊነት - አንድ ሉዓላዊ የሆነ ተቋም የራሱን ፣ ስትራቴጂካዊ መረጃዎችን ወይም ሐብቶችን መጠበቅ እንድትችል ይረዳሃል [....] ይህ ደግሞ የራስን የዲጂታል መሰረተ ልማት መገንባትህ ስለማይቀር ለሀገር ውስጥ ስራ ፈጠራዎችም  እድል ይሰጣል’’ ብሏል - ከፍተኛ የሶፍትዌር ኢንጅነር እና የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት አበልፃጊዉ  አቤል በነበሩ ፡፡ይህም በመረጃ ሉዓላዊነት ላይ አዎንታዊ ሚናን እንደሚጫወት ባለሙያው ተናግረዋል ፡፡ የሳይበር ጥቃት አይነቶች እንዴት ያሉ ናቸዉ ?  በታዳጊ ሀገራት ያሉ  አገልግሎት ሰጪዎች  የሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ ክፍትቶቻቸዉ ምንድን ናቸው ? ለጥያቄዎቹ መልስ የሚሆኑ እና ሌሎች ሐሳቦችን በሶቨርኒቲ ሶርስስ ላይ ይከታተላሉ።

6/9/25 • 60:00

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፉ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲዋን በማሻሻል እየሰራች ነው ። ለዚህም ከሩሲያ ጋር ትብብርን በመፍጠር ማርሽ ቀያሪ  አጋርነትን መሥርታለች። ትብብሩ ከሮቦቲክስ እስከ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ድረስ በደቡባዊው ዓለም ውስጥ ፈጠራን እንደ አዲስ  ያስተዋውቃል። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችንም በጉዳዩ ላይ  የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ  ባህሩ አባስን ወደ ስፑትኒክ ስቱዲዮ ጋብዞታል ። የባለሙያው ዕይታ፡“ይህ የቴክኖሎጂ ጉዳይ ብቻ አይደለም -  የሉዓላዊነት ጉዳይም እንጂ። ኢትዮጵያ የሠው ሰራሽ አስተውሎት አቅሞቿን ወደ ላቀ ደረጃ ማስፈንጠር ትችላለች፣ ሩሲያም በአፍሪካ የዲጂታል ምጣኔ ሐብት ላይ ያላትን ተሳትፎ ታረጋግጣለች” ሲል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያው  ባህሩ አባስ ተናግሯል።ከጂኦ ፖለቲካ ባሻገር፡ በኢትዮጵያ በሠው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ማዕቀፍ ፣ የሩሲያ  እና  ብሪክስ አባል ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን  መሠረት ያደረገ አጋርነት የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ተራማጅ ዘርፍ እንዲገነቡ ያነሳሳቸዋል።🎙በሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕርግራም የሚቀርበውን ሙሉ መሠናዶ ለመከታተል ዝግጁ ነዎት?

6/11/25 • 60:00

በአፍሪካ ሰማይ መልካም ዕድሎች ያንዣብባሉ! የአቪዬሽን ዘርፉ ለጠንካራ እድገት ተሰናድቷል፣ በዚህም ለአየር መንገዶች፣ ባለሃብቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ ዕድል ፈጥሯል። ነገር ግን ይህን ከፍታ የሚያነሳሳው ምንድነው - ደግሞስ ምን ወደኃላ ሊጎትተው ይችላል?በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ መሠናዶ በጥልቀት ለመወያየት የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያው ዮናታን መንክር በእንግድነት ጋብዘናል።የአቪዬሽን ዘርፉ ምን ያህል ሁነኛ መሣሪያ ስለመሆኑ ባለሙያው ዮናታን ሲያብራሩ፡-  “አቪዬሽን ወይም የአየር ትራንስፖርት የሚሰጠው ነገር የመንገደኞችን ሰዓት መቀነስ ነው። ይህ ዕውን የሚሆነው የአየር ትራንስፖርት ለንግድ  አገልግሎት  ተደርጎ ሲወሰድ ነው። ነገር ግን አቪየሽኑን በአጠቃላይ ከወሰድን፣ ብዙ ነገሮችን ማንሳት እንችላለን፣ የህክምና ቱሪዝም ፣ የግብርና አቪዬሽን ፣ በዋነኛነት  ለቱሪዝም ተግባራት ፣ ለአየር ካርታ ስራ እና ለምትለው ስራ ሁሉ አጠቃላይ የአቪዬሸን ዘርፉ ትልቅ ጥቅም ነው ያለው''  ብለዋል ።ዮናታን ዘርፉ በአህጉሪቱ እንዳይጎለብት ስለሚያደርጉት ማነቆዎች በተመለከተ ሲያስረዱ ፦ “የአፍሪካ አቪዬሽን ዘርፍ ዕድገት ማነቆ ከሆኑ ነገሮች መካከል መሠረ ልማት አንዱ ነው። መሰረተ ልማት ሲባል የረጅም ጊዜ ትስስር ነው። ይህ የአውሮፕላን ማረፊያ ወይም በዙሪያው የሚኖሩ ፋሲሊቲዎችን መገንባት ማለት አይደለም። ስለዚህ መንገዶች እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው።ይህም ከአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል የሚያልፍ መንገደኛ የሚጓዝበት ነው ''  ሲሉ ተናግረዋል በአፍሪካ በዘርፉ ያሉ ትብብሮችም ፣  ከኢትዮጵያ ጠቃሚ ልምዶች የሚቀሰምባቸው ቢሆኑ አዋጭ ስለመሆኑ የአቪዬሽን ባለሙያው ዮናታን መንክር  ተናግረዋል። “አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የጎለበተ የሠው ኃይልና ቴክኖሎጂ እንዲኖራቸው በአፍሪካ ቀዳሚ ወደሆነው  የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠጋታቸው ጥሩ ማሳያ ነው። ነገር ግን ይህ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ነው መሆን ያለበት። ስለዚህ ሀገራት በቴክኖሎጂ፣ በምጣኔ ሐብትና በሰው ኃይል አጋርነት ላይ እንዲተባበሩ ፍላጎት ሊኖር ይገባል።  እነዚህ ነገሮች ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪ እድገት እና ልማት በጣም ቁልፍ ናቸው” ብለዋል።ስለ አቪዬሽን ዘርፉ የበለጠ ለመረዳት በስፑትኒክ አፍሪካ ተሰናድቶ የሚቀርበውን ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሰናዳውን የሶቨርኒቲ ሶርስስ መሠናዶ ይከታተሉ ።

6/17/25 • 60:00

ፍሪካ ከምትጠቀመው ክትባት በራሷ የምታመርተው 1% ብቻ መሆኑን ያውቃሉ? የአህጉሪቱ የጤና ደህንነት መሠረት ያደረገው የውጭ ድጋፍ ላይ እንደመሆኑ እርምጃ የመውሰጃ ጊዜው አሁን ነው!የሶቨርኒቲሶርስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች ሀሳባቸውን እንዲያጋሩን በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨቅላ ህፃናት ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ጡረኝ ስዩም ን ጋብዟቸዋል።ዶ/ር ጡረኝ ሀገር በቀል ክትባት ማምረት የሚያስፈልግበት ምክንያትን ሲያስረዱ፡“ክትባት በብዙ መጠን ማምረት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ምክንያቱም አቅርቦት አለመኖር ከማነቆዎች መካከል አንዱ ስለሆነ። ስለዚህ፣ በራሳችን አውድ የክትባት ምርት ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ብዙ ሥራዎች ፣ ኢንቨስትመንት እና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ነው። ” ሲሉ ተናግረዋል።የአፍሪካ ሀገራት በጋራ ተጣምረው ክትባት ማምረት ስለሚችሉባቸው መንገዶች  ዶ/ር ጡረኝ ሲያብራሩ :-“የአፍሪካ ሀገራት አንድ ላይ በመሆን ይህን ችግር መፍታት እንችላለን። ነገር ግን ምንም እንኳ አንድነት ብንፈጥርም፣ በቁርጠኝነት  የረጅም ጊዜ የጋራ መግባባት የሚፈልግ ጉዳይ ነው። እናም እንደጠቀስኩት ለክትባት ምርትና ልማት ብዙ መመዘኛዎች አሉ።  ስለዚህ ግቦቹን ለማሳካት እነዚያ ሁሉ መመዘኛዎቾ ሊታቀዱና ሊሰሩ ይገባል።'' ብለዋል።➡️ የጅምላ ምርት - እጥረትን ለመቅረፍ ➡️ የፓን አፍሪካ ትብብር - ለረጅም ዘመን ስኬት➡️ ኢንቨስትመንትና ቁርጠኝነት - ራዕይን ወደ እውነታነት ለመለወጥስለሀገር በቀል ክትባት ምርት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የበለጠ ለመረዳት ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን ፣ የሶቨርኒቲ ሶርስስ  ሙሉ ፕርግራምን ይከታተሉ።  ሙሉ ፕርሮግራሙን ለማድመጥ ዝግጁ ነዎት?

6/18/25 • 60:00

ጥበብ ገለፃ ብቻ አይደለም — በዓለም መካከል ድልድይም ጭምር እንጂ!  ከባህል እስከ ሰላም ግንባታ፣ ፈጠራ የሰው ልጆችን ፍላጎት አንድ ላይ ያጣምራል።

6/20/25 • 60:00

የቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ንቅናቄ እንዲጀመር ምክንያት የሆነው እ.ኤ.አ ሰኔ 24 ቀን 1859 ፤ በሰሜን ኢጣሊያ ለንግድ ሥራ ሲጓዝ የነበረው አንሪ ዱና በጣሊያን ሶልፈሪኖ የተመለከተው አሰቃቂ እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ነበር። ክስተቱ ዓለም አቀፍ የርህራሄ መልክን ፈጥሮ አልፏል።ዛሬ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችን ይህንኑ ዕለት ሲያስብ ፣ የደጃዝማች ባልቻ የሩሲያ ቀይ መስቀል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አንድሬይ ቭላድሚሮቪች ጎንቻሮቭን በእንግድነት ጋብዟቸዋል።

6/24/25 • 30:00

የማረጋጋት ተልዕኮዎች ወደ ረጅም ጊዜ የወታደራዊ ሰፈራ፣ የዕዳ ወጥመድ እና አስገዳጅ የዲጂታል ቁጥጥር ስርዓቶች ተቀይረዋል።  ምዕራባዊያን በአዲስ መልክ አፍሪካን ለመቆጣጠር እየተንቀሳቀሱ ይሆን?የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለምዕራባዊያን ጠንካራ የኃይል ስልትና ስለዳግም ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት ክቡር ገና - የኢኒሼቲቭ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተርን ጋብዟቸዋል።

6/27/25 • 30:00

ከዕውቀት ሽግግር እስከ ኢነርጂ ሉዋዓላዊነት፣ ብሎም እስከ ጤናው ዘርፍ - አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል።የኒውክለር ሳይንስን ለሰላማዊ ጉዳይ የማዋል ቁርጠኝነት በጤናው ዘርፍ አንድ ብሏል።የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለኒውክለር ኢነርጂ በኢትዮጵያ እንዲሁም በዘርፉ ከሩሲያ ጋር ስላለ ትብብርና አጋርነት በጥልቀት ለመወያየት ዶ/ር እምሻው ዳምጠው፣ በኢትዮጵያ የኒውክለር ኢነርጂ ሶሳይቲ ዳይሬክተር እንዲሁም ዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል ፣ የኒውክለር ፊዚክስ ስትሪም ተባባሪ ፕሮፈሰርን ጋብዟቸዋል።

7/1/25 • 60:00

ኢትዮጵያ እንደ ጁቡቲ እና ሱዳን ላሉ ጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ታቀርባለች። ወደ ታዛንያም የሙከራ አቅርቦቱ ተጀምሯል — ሀገሪቷ የብሪክስ አባል እንደመሆኗ ከዚህ የላቀ የኃይል አቅርቦት ለማድረስ ትተጋለች።የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከቀጠናዊ ሀገራት ጋር ያለው ትብብርና የጋራ ዕድገት፣ በዘርፉ ከብሪክስ አገራት በተለይም ሩሲያ ጋር ስላለ ትብብርና አጋርነት በጥልቀት ለመወያየት ሞገስ መኮንን፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተርን ጋብዟቸዋል።

7/2/25 • 30:02

የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ የማዕድን ሀብቶች አላት ፤ ከእነዚህም መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም እና ሌሎቹ በምድሯ ይዛለች።ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ትናንት ለምክርቤት አባላት ማብራሪያ ሲሰጡ ማዕድንን በተመለከተ "ኢትዮጵያ ከፍተኛ ማዕድን ሀብት ያላት ሀገር ናት [...] ዘንድሮ ከወርቅ ብቻ [አምና ከነበረው በ10 እጥፍ ዕድገት]  3.5 ቢሊየን ዶላር ከዉጪ ንግድ አግኝተናል" ብለዋል።የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ማዕድን እና ጂኦሎጂካል ሀብት ፍለጋ ከሩሲያ ጋር ስላለው ስትራቴጂያዊ ትብብርና ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ዶ/ር በቀለ አየለ በዳዳ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ጂኦሎጂ ዲፓርትመንት ረዳት ፕሮፌሰር እንዲሁም በማዕድን ዘርፎች አማካሪ ሙስጠፋ ሻይኮ ሼኩን ጋብዟቸዋል።

7/4/25 • 60:04

በአፍሪካ በተንቀሳቃሽ ስልኮችና መሠል መሣሪያዎች ላይ በሚጫኑ መተግበሪያዎች አማካኝነት የሚሳለጡ የንግግድ ልውውጦች በፍጥነት እየጎለበቱ ነው። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ በኤክትሮኒክ መር ገበያ ስለሚሳለጡ የፋይናንስ ልውውጦች፣ በብሪክስ ሀገራት መካከል ስላለ መልካም ዕድልና የአፍሪካ ሀገራት ትብብር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ማርቆስ ጥላሁን፣ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ባለሙያ እና ፕሮሞተርን ጋብዟቸዋል።

7/8/25 • 60:04

የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የድምፅ አስተውህሎት በተለይም በሠው ሠራሽ አስተውህሎት የሚታገዘው መተግበሪያ እንዴት የአፍሪካን ቋንቋዎች በዲጂታል መንገዱ ተደራሽና እጅግ ጠቃሚ እንደሚያደርግ፣ በዘርፉ የሀገራት ተሞክሮና እንደ ሩሲያ ካሉ በዘርፉ የመጠቁ ሀገራት ጋር የሚደረግ ትብብር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ቅዱስ ያሬድ፣ የሀሳብ ኤ አይ - የድምፅ ሠው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያ ተባባሪ መሥራችን ጋብዞታል።

7/9/25 • 60:00

በአፍሪካ ሰፊ የህዝብ ቁጥር የሚይዘው ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል ከሥራ አጥነት ለማላቀቅ መንግስታት አዳዲስ የሥራ ፈጠራዎችን ሊያበረታቱ እንደሚገባ ይታመናል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለአፍሪካ አህጉር የሥራ ፈጠራ እና የሀገራት የጋራ ቅንጅት በጥልቀት ለመወያየት የኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል አህመድን ጨምሮ ሌሎች የአህጉሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 በተካሄደው በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ጉባኤ ላይ አነጋግሯቸዋል።

7/10/25 • 30:00

የተለመደ ታሪክ አይደለም። ግን ሁሌም ከፍ ብሎ የሚደመጥ የኢትዮጵያ ልጆች ድንቅ የህክምና ገድል ነው። የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጣብቀው የተወለዱ ልጆችን በስኬታማ የቀዶ ህክምና እንዲለያዩ አድርጓል።የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃግብሩ ተጣብቀው ስለተፈጠሩ ህፃናት፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቡድን ስለተደረገ ስኬታማ የቀዶ ህክምና በጥልቀት ለመወያየት የህፃኑ እናት ሙሉ ግርማን እና በሆስፒታሉ የጨቅላ ህፃናት ቀዶ ህክምና ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አባይ ጎሳዬን አነጋግሯቸዋል።

7/14/25 • 30:00

ኢትዮጵያ 96% የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጯ ታዳሽ ኃይል ነው። ሶቨርኒቲ ሶርስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ታዳሽ ያልሆኑ ሐብቶችን የመቀነስ አስፈላጊነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊዚካል ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው አዳምወርቅ (ዶ/ር) ጋብዘናቸዋል።

7/17/25 • 60:00

"በዶላር ወይም የራስህ ባልሆነ ምንዛሬ ስትገበያይ [...] ኪሳራ ስለሚኖር አንዳንድ ጊዜ እነዚህ አስቸጋሪ ቅድመ-ሁኔታዎች ናቸው። ስለዚህ ተግዳሮቶቹን ለመቅረፍ አዲሱ የልማት ባንክ ወይም ብሪክስ በብሔራዊ ገንዘቦች ለመገበያየት ሁነኛ መላ ዘይዷል"ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የአፍሪካ ሀገራት ከብሪክስ አባላት ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ የኢትዮጵያና ህንድ ግንኙነትን አብነት አድርጎ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ሬይን ጋብዟቸዋል።

7/17/25 • 30:00

"ኢትዮጵያ በነጻነት ፋና ወጊነት አፍሪካን ነፃ የማውጣት ትልቅ ሚናን ተጫውታለች። በ1960ዎቹ ለነፃነት የሚደረግ ትግልን ደግፋለች — ማንዴላ በድፍረት የአፓርታይድ አገዛዝን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ባይታገል፣ የነፃነት ጮራ ለመፈንጠቅ ያለእርሱ ነገሮች ትንሽ ይከብዱ ነበር - ሲሉ የታሪክ ምሁሩ ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ ተናግረዋል።"በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት አቅራቢው የማንዴላ ዓለምአቀፍ ቀንን መሠረት አድርጎ በበርካታ ጉዳዮች ከታሪክ ምሁሩ ፕሮፈሰር አህመድ ዘካሪያ እና የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ጆሴፍ ኒዲኩሙኪዛ ጋር ተወያይቷል።

7/18/25 • 60:00

“ለምን እንደሆነ? አሜሪካ ለምን [በድርድር ሂደቱ] እንድትሳተፍ እንደሚፈልጉ አይገባኝም። ውሃው የሚፈሰው በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ ነው። ዉሃው የሚፈሰው በእነዚህ በሶስቱ ሀገራት ዘንድ ነው። ወንዙ [አባይ] ከአሜሪካ ተነስቶ ወደ ግብፅ የሚሄድ ነው ያስመሰሉት። ስለዚህ በአብዛኛው የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ የሶስተኛ ወገኖች ተሳትፎ አይበረታታም ምክንያቱም ሶስተኛ ወገኖች ስጋቶችን፣ የሀገራትን ጭንቀትና ጥቅምም አይረዱም።''በዚህ #SovereigntySourcess የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት አቅራቢው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ የሰጡትን አስተያየት መነሻ በማድረግ የውኃ ሐብት ኤክስፐርት እና አማካሪው ፈቅ አህመድ ነጋሽን ጋብዟቸዋል።

7/21/25 • 30:00

የባህል ገፆች፣ መንፈሳዊ፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ባህሎችን መለዋወጥ መቻል ትልቅ ዕድል ነው። ይህም ጸሐፊያን በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለ የቀደመ መስተጋብራዊ ልማትን በአንክሮ እንዲፈትሹ ያደርጋቸዋል።''በዚህ Sovereignty Sources የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት፣ አቅራቢው ስለ ቴአትር ጥበብ፣ የኢትዮ - ሩሲያ ግንኙነትን ለማጠናከር ስላለው ፋይዳ ለመወያየት ጳውሎስ አዕምሮ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲያትሪካል ጥበባት እና የባህል ማዕከል አካዳሚክ ዲን ጋብዟቸዋል።

7/22/25 • 60:00

"ዲጂታል መፍትሄዎች የጤና አጠባበቅ ስርዓቱን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን አገልግሎት የምንሰጥበትን መንገድ በአዲስ መልክ ፈጥረውታል። በዚህ ሂደት ውስጥ ዲጂታል አገልግሎቱ የጤና አሰጣጥ ስርዓትን የሚያሻሽልባቸው በርካታ ተግባራዊ መፍትሔዎቼ አሉት።"በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት አቅራቢው ስለዲጂታል መር የጤና አልግሎት ስርዓትና የስታርታፖች ሚና በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ጋይኒኮሎጂክ ኦንኮሎጂስት እና የዊኬር ኢንተገሬትድ የጤና ኔትወርክ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቤተል ደረጄን ጋብዟቸዋል።

7/24/25 • 30:00

“ባለን መረጃ መሠረት የጉበት በሽታ ከባድ ችግር ነው። ምናልባት ተኝቶ ህክምና ከሚገቡት 12% የሚሆኑ ታካሚዎች ከጉበት በሽታ ቫይረስ ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በሆስፒታል ውስጥ የሟቾችን መጠን በተመለከተ 30 ወይም 31% ሟቾች በቀጥታ ከጉበት በሽታ ቫይረስ ጋር የተገናኙ ናቸው።” በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም፣ አቅራቢው የዓለም የጉበት በሽታ ቀንን መሠረት በማድረግ በዓለም ላይ ገዳይ ከሆኑ ተላላፊ በሽታዎች አንዱ ስለሆነው የጉበት በሽታ እና ቫይረሱን ለማጥፋት ኢትዮጵያ እያደረገች ስላለችው ትግል ለመወያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨጓራ እና ሄፓቶሎጂስት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ረዘነ በርሄን ጋብዟቸዋል።

7/28/25 • 30:00

“ኢትዮጵያ ከሮሳቶም ጋር በመደራደር ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች ሀገራት ባለሙያዎች እና ተማሪዎች ክፍት የሚሆን፣ የኒውክሌር ማሠልጠኛ ማዕከል ወይም የነፃ ትምህርት ዕድል ፕሮግራም ማቋቋም ትችላለች'' ሲሉ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የኒውክለር ፊዚክስ ተመራማሪው ቸሬ ሲሳይ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የኒውክለር ኢነርጂ ትግበራ በጤናው ዘርፍ እና ሌሎች ጉዳዮች ለመወያየት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው ቸሬ ሲሳይ እና በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የኒውክለር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኩሩቤል ተስፋዬን ጋብዟቸዋል።

7/30/25 • 60:00

“የአፍሪካ አህጉር የበርካታ ሀገር በቀል የምግብ ስርዓቶች ባለቤት ናት። እነዚህ የምግብ ስርዓቶች በእምቅ እውቀት፣ በዘላቂና ዘመን ተሻጋሪ አውዶች የተሞሉ ናቸው'' ሲሉ ሼፍ ፋትማታ ቢንታ ተናግረዋል። 🎙 በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ስለአፍሪካ የምግብ ስርዓትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት እንደ ሼፍ ቢንታ ያሉ ሙያተኞችን ጨምሮ በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎችና የባህል መሪዎችን ጋብዟቸዋል።

8/1/25 • 60:00

"ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዝሃ ህይወት ምንጭ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ነች። ለዚህም ከ125 ሜትር የባህር ወለል በታች፣ ዳሎል እስከ ከፍተኛው የተራራ ጫፍ ወይም 4620 ሜትር የሚረዝመው ራስ ዳሽን ተራራ በአብነት ይጠቀሳሉ። በደን ብዝሃ ህይወት ረገድ በርካታ የዱር እንስሳት፣ እፅዋት፣ አዕዋፋት እና ሌሎቹ ሀገሪቷን ልዩ እንድትሆን አድርገዋታል።”በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የዱር እንስሳትን እና ቱሪዝምን የሚደግፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የብዝሃ ህይወት እና አረንጓዴ እድገት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የብዝሃ ህይወትና አካባቢ ጥበቃ አማካሪው ስሜነህ አድማሱን ጋብዟቸዋል።

8/5/25 • 30:00

"የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከተመለከታቸው 33 ጉዳዮች መካከል 90% በላይ የሚሆኑት የደቡባዊ ዓለም ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። በአጋጣሚ ብቻ የሆነ አይደለም፤ ይልቁን የምዕራባውያንን ጥልቅ አድልዎ የሚያሳይ ነው። አንድም ክንደ ፈርጣማ የምዕራቡ ዓለም መሪ ወደ ፍርድ ቤቱ አልቀረበም፣ ይህም እምነትን ያዳክማል። ስለዚህ ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ህጎች እንዳሉ ያረጋግጣል።" ሲሉ የማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት ምሁሩ መሀመድ አወል ሀጎስ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ስለፓን አፍሪካኒዝም፣ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አድሏዊ ፍትህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በጥልቀት ለመወያየት በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት ምሁሩ መሀመድ አወል ሀጎስን ጋብዟቸዋል።

8/7/25 • 30:00

'የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ቦታዎች ላይ ቢፈጠርም በአብዛኛው ከባህር ወይም ከውቅያኖስ በታች የሚፈጠር ነው፡፡ አትላንቲክ ውስጥ አለ፣ ህንድ ውቅያኖስ ውስጥ አለ፣ ልዩ ልዩ ቦታ አለ፡፡ በደንብ ግን የመፈጠሩ ሂደት የሚታየው ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሰምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው ።'' የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በርዕደ መሬት እና ተያያዥ ጉዳዮች ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ጋብዟቸዋል።

8/11/25 • 60:12

“በውጤቱ እኛንና መሰል ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ አሁን በአብዛኛው በተለያዩ የህክምና፣ የእርሻ እና ሌሎች ዘርፎች የሚሰሩ የቀድሞ ተማሪዎች አሉ፤ በፖለቲካው ረገድም ትልቅ ቦታ የደረሱ ሰዎች አሉ፤ በከፍተኛ የስልጣን ወይም የሥራ አመራር ደረጃ ላይ የተቀመጡ ናቸው፡፡ በዚህም በአገሪቷ የተማረው የሰው ኃይል ቁጥር እየጠነከረና እየሰፋ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ በምርምሩም የተሰማሩ ሰዎች አሉ ዛሬም ድረስ - ሲሉ ዶ/ር ክብሩ ቸርነት ተናግረዋል”በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በየጊዜው እየጨመረ የመጣው ሩሲያ ለወጣት አፍሪካዊያን ተማሪዎች እያመቻች ያለችው የትምህርት ዕድልና ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የቀድሞ የሶቭየት ኅብረት ተማሪዎች ዶ/ር ክብሩ ቸርነት እና ዶ/ር ደረጄ ጌታሁንን ጋብዟቸዋል።

8/13/25 • 60:00

"ከአውሮፓውያኑ እና ዩክሬን የበለጠ አስፈላጊው የሩሲያ እና የአሜሪካ ንግግር ስለሆነ ዩክሬን ብቻ ሳትሆን አውሮፓውያኑም ከዚህ ሂደት ውጭ ናቸው። ስለዚህ  ትራምፕ ራሳቸውን አጋር ለማድረግ ከሌሎች ኃይሎች የበለጠ ጠንካራ ከሆነችው ሩሲያ ጋር ለመነጋገር ብልህ መሆንን የተረዱ ይመስለኛል"  ሲሉ የታሪክ ምሁሩና የፖለቲካ ተንታኙ ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ የዓለም መሪዎች ቭላድሚር ፑቲንና ዶናልድ ትራምፕ በአላሳካ በሚያደርጉት ተጠባቂ ስብሰባ በሰፊው ይዳስሳል።በስብሰባው የሚነሱ አንኳር ጉዳዮች፣ የግንኙነታቸው ፖለቲካዊ አንድምታና ሌሎች በርካታ ተያያዥ ሀሳቦች ለመወያየት ፕሮፌሰር አየለ በክሪ፣ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪ እንዲሁም ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ ፣ የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ እና ጉምቱው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን ጋብዟቸዋል።

8/15/25 • 60:00

“ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ይልቅ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያሸነፉ ይመስለኛል። ትራምፕ በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ዩክሬንን በተመለከተ የታዘብነው አንድ ነገር፣ በምዕራባውያን ኃይላትና አጋራት መካከል ትልቅ ክፍፍል ተፈጥሯል። ቀደም ባሉት ጊዜያት በባይደን አስተዳደር ዘመን አውሮፓውያን ከዋሽንግተን የሚወጣውን ማንኛውንም ነገር በጥብቅ ይከታተሉ ነበር። አሁን ግን ግልጽ ተቃውሞ አይተናል። ዜለንስኪ ቢሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ይቃረናቸዋል። ስለዚህ አንድ ግልጽ የሆነው ነገር በምዕራባውያን አጋራት መካከል መለያየት ያለ ይመስለኛል " ሲሉ ምሁሩና የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶ/ር አስናቀ ከፋለ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ የዓለም መሪዎች ቭላድሚር ፑቲንና ዶናልድ ትራምፕ በአላሳካ ያደረጉት ውይይትን በስፋት ያስቃኛል።በመሪዎቹ ጉባዔ የተነሱ አንኳር ጉዳዮች፣ የግንኙነታቸው ፖለቲካዊ አንድምታ፣ ከጉባዔው መነሻነት ወደፊት የሚጠበቁ ጉዳዮችና ሌሎች በርካታ ተያያዥ ሀሳቦችን ለመወያየት ምሁሩና የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶ/ር አስናቀ ከፍለ፣ የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ እንዲሁም ጉምቱው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን እንዲሁም ሱዳናዊው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ፣ ዲፕሎማትና ጋዜጠኛው መኪ ኤልሞግራቢን ጋብዟቸዋል።

8/18/25 • 60:00