Show cover of Drum of Changes

Drum of Changes

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power.Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.

Tracks

የዓለም አቀፉ ደቡብ ጋዜጠኞችም ዓለም አቀፍ ክስተቶችን ከራሳቸው ታሪክ፣ ፍላጎት እና እውነታዎች አንፃር በመቃኘት የተዛነፉ ትርክቶችን ለማቅናት የጋራ ጥረቶችን ጀምረዋል። "ላለፉት አስርት ዓመታት ዓለም አቀፍ ዜናዎች ከአንድ አቅጣጫ የሚመጡ እና የአንድ ወገን ሐሳብን የሚያንቀባርቁ ነበሩ … በአንፃሩ ደግሞ አሁን ያለንበት ወቅት የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ንቃት ጎልቶ ይስተዋላል … የዓለም ታሪክ ርዕሰ አንቀጽ እንጂ የማንኛውም ታሪክ ዳራ መሆንን እምቢኝ ያሉበት ወቅት ነው" ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ት/ት ክፍል መምህርና እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አየለ አዲስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን የደቡቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ስለሚያደርጓቸው ትብብሮች በቀዳሚነት እንቃኛለን። ለዚህም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ት/ት ክፍል መምህርና እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አየለ አዲስ (ዶ/ር) አብረዉን ቆይታ አድርገዋል። በሁለተኛው ጥቅራችን ደግሞ በአፍሪካ የዲጂታል ክፍያ ስረዓት እጣፈንታን በተመለከተ፣ በቴንድኤክስ አዲስ አበባ 2026 ጉባኤ ላይ ተገኝተን ኮምፑሊንክስ የተሰኘ ኩባንያ ቢዝነስ ዳይሬክተር የሆኑትን ቻውላ ጋናትራን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ

2/9/26 • 60:00

“ ከቆዳችን በታች ሁላችንም አንድ አይነት መሆናችንን እናያለን … ፖለቲከኞች ለራሳቸው ዓለማ ከዚህ የተለየ ኃቅ ሊያሳዩን የመቻል አቅማቸዉን አሳንሼ ግን ማየት አልፈልግም … ነገር ግን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ሩሲያ ወይት ሌላ ቦታ ብንኖር ሰዎች ሁሉ አንድ ዘር ነን” ሲሉ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ፣ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ ተመራማሪ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እጅግ የተሟላ እና ጥንታዊ የሆነችውንና ከ3.3 ሚሊየን በላይ እድሜ ያላት የሰላምን (አውስትረሎፒቲከስ አፋረንሲስን) እና በቅርቡ የተገኘውን የ 2.6 ሚሊየን እድሜ ባለቤት ፓራንትሮፐስ ጨምሮ የብዙ ግኝቶች እና ምርምሮች ባለቤት፣'ምድረ ቀደምት (ላንድ ኦቭ ኦሪጅን)' የሚለውን መጠሪያ ያስተዋወቁ እና በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ተመራማሪ መምህር፣ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድን በእንግድነት ጋብዟቸዋል።በቅርቡ ያገኙትን ቅሪተአካል (ፓራንትሮፐስ) መነሻ በማድረግ ስለሰው ዘር አመጣጥ ፣ኢትዮጵያ ስላላት ማዕከላዊ ስፍራም እናወጋለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

1/29/26 • 60:00

የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የባህል ቅርሶች ከአህጉሪቱ ውጭ ይገኛሉ። ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሙዚየሞች ብቻ ከ500,000 በላይ የአፍሪካ ቅርሶችን ይዘዋል።ከእነዚህም አብዝኃኛዎቹ በቅኝ ግዛት ዝርፊያ፣በአስገዳጅ ሁኔታዎች ወይም በሕገ-ወጥ ዝውውር የተገኙ ናቸው። "ከአገራችን ተዘርፈው ተወሰዱ ቅርሶቻችን በክፍያ መልሰን እንድንወስድ መጠየቃችን አሳዛኝ ነገር ነው። እነዚህን ቅርሶች የያዙ ሙዚየሞች ወይም የግል ቅርስ ሰባሳቢዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመልሷቸው እናበረታታለን"ሲሉ የሺ ካሳ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አባተ ጎበና (ዶ/ር) በበኩላቸው "በመቅደላ ጦርነት ወቅት ወደኢትዮጵያ የመጡ እንግሊዛውያን፣ አስቀድመው ስለኢትዮጵያ ውድ ቅርሶች ያውቁ ነበር። ቅርሶቹን ለመዝረፍ በጀት ተመድቦላቸው የመጡ ባለሞያዎችም የሀገሪቱ ቅርሶች ዘርፈዋል።[...] ምዕራባዉያን [በማንኛውም መልኩቢመጡ] ባዶ እጃቸውን ግን አይመለሱም ነበር።" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በምእራቡ ዓለም እስረኛ የሆኑ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ቅርሶችን ጉዳይ እንመረምራለን። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

1/29/26 • 25:59

''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳው መካከል የፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎች ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው '' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ በንግድ እና ኢኮኖሚ ላይ ያለው በጎ ተፅዕኖ በተመለከተ ከአሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶክተር ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ጉዳይን በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድቤት ፊት ስለማቅረብ ከያዛቸው ውድነህ የኢንቫይሮመንታል ጂዮግራፈር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና አዳፕቲሽን ባለሙያ፣ መምህርና ተመራማሪ ጋር ቃኝተነዋል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ

1/28/26 • 60:00

"አፍሪካውያን ሉዓላዊነትን የምንገልፅበት እና የምንረዳበት መንገድ ምዕራባውያን በ'ዌስታፋሊያ' ሰምምነት መሰረት ከሚነግሩን የሉዓላዊነት እሳቤ የተለየ ነው።[...] አፍሪካውያን የወረስነውን የምዕራቡን ዓለም ሉዓላዊነት መንገድ በመተዉ [...] ወደውስጥ መመልከት፣ የጋራ ሀብቶቻችንን በጋራ ስለመጠቀም ማሰብ አለብን።" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ዛሬ በድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ጥንቅራችን 'አፍሪካ ሀብቶቿን በጋራ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያለውን ምዕራብ ተኮር እሳቤ መተው ስትችል ነው' የሚል መከራከሪያ ከሚያቀርቡት እና በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደርጋል። በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የከንቲባዎች ምክክር መነሻ በማድርግ የአፍሪካ ከተሞችን እና የእድገት ጉዟቸዉን ይዳስሳል። ለዚህም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ እንግዶች ጋር ቆይታውን ያደርጋል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

1/27/26 • 60:00

"በዩክሬን ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ [አሜሪካኖቹ] ሙሉ በሙሉ እንደሚረዱ እርግጠኛ ነኝ። ምዕራባውያን በተለይም አውሮፓውያን የሞራል ኪሳራ እንዲሁም በወታደራዊ አቅርቦት እና ቴክኖሎጂ አቅማቸው ላይ በዩክሬን ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ተረድተዋል። የትራምፕ አስተዳደርም በዩክሬን ውስጥ ማን የበላይ እንደሆነ በትክክል ያውቃል። ስለዚህ ስለ ሰላማዊ መፍትሄ በቁም ነገር ማሰባቸው ተገቢ ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት በጥር 20፣ 2026 (እ.ኤ.አ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ 2025 ዲፕሎማሲያዊ ግምገማ እና ለ2026 የተያዘውን ውጥን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ዳዊት መዝገበ ምልከታቸውን ያጋሩናል። በሁለተኛው ክፍል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የአህጉሪቱን የግብርና ዘርፍ ለማበልፀግ ስለተነደፈ እቅድ እንዳስሳለን። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ማንደፍሮን (ዶ/ር) አነጋግረናል።በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

1/22/26 • 60:00

"አባቴ፣ ለኢትዮጵያ ከአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን የተሻለ አጋር የለም ብሎ ያምን ነበር … አባቴ በአሜሪካን ሀገር በትምህርት ላይ ሳለ ጥቁር በመሆኑ ብቻ የደረሰበትንም አልረሳም … እነዚህ ሁኔታዎች የፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ላይ እንዲበረታ አድርገዉታል"- ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬዉ ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ታላቁን ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ከተማ ይፍሩን እንዘክራለን። ለዚህም በቅርቡ "ከተማ ይፍሩ፡ የሰላም፣ የእድገት እና የአፍሪካ አንድነት ሻምፒዮን" በሚል ርዕስ አባታቸዉን የሚዘክር መጽሐፍ ያሳተሙት ልጃቸው አቶ መኮንን ከተማ ይፍሩ እንግዳችን ናቸው። ሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ፣ በቅርቡ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከበረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጉዳዩ አድርጎታል። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የኢትዮጵያ ታሪክ እና ማህበረሰብ ጥናት ማዕከል ኃላፊ የሆኑትን ዘላለም ተፈራን (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

1/16/26 • 60:00

“አፍሪካውያን የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን እንዲጠቀሙ ከሚገፋፉ ምክያቶች መካከል የምዕራቡ ዓለም የውበት መስፈሪያ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል[…]ምርቶች እንዲሸጡላቸውም በማህበራዊ ሚዲያ የውበት መስፈርትን የሚያወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማትም አሉ” ሲሉ በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በመላው አፍሪካ፣ የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መማጣቱን በማንሳት ጤና እና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ቀውስ እንቃኛለን። በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ዙሪያ ሞያዊ ምልከታቸዉን እንዲያጋሩንም በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ ከ 12,000 ዓመታት በኋላ እንደፈነዳ የተነገረለትን የሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የጠፈር ሳይንስ እና የስነ ፈለክ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑትን ፕሮፌሰር አታላይ አየለን አነጋግረናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

12/31/25 • 60:00

ሶማሌላንድ ከእስራኤል ያገኘችው የሀገርነት እውቅና በተወሰነ ደረጃ ህጋዊነትን እንድታገኝ ቢያስችላትም፣ ከሶማሊያ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከሌሎች ሀገራት እየተሰጠው ያሉ ምላሾች በመጭው ጊዜያት የግዛት አንድነት ጥያቄዎች ማዕከላዊ ሆነው እንደሚቆዩ ያሳያል። "እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና ከዓለም አቀፍ ሕግ ይልቅ፣ ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ ይታያል … በቀጣናው ሶማሊላንድ አዲስ ተዋናይ ሆና ብቅ ልትል ትችላለች፣ አዲስ ዓይነት የኃይል አሰላለፍም ሊፈጠር ይችላል" ሲሉ ጠበቃ፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን እንመለከታለን። በቀዳሚው ጥንቅራችን ከሰሞኑ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችዉን የሀገርነት እውቅና እንስተን አንድምታዎቹን እንመለከታለን። ለዚህም ኢትዮጵያዊውን ጠበቃ እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን በማንሳት በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባ የሚኖረዉን ሚና እንቃኛለን። ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር፣  የሺዓለም ገዛኸኝ (ዶ/ር) በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የኮምፒዉተር ሳይንስ ትመህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር፣ እና አቶ አበበ ፀጋዬ በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የአይሲቲ ዋና ዳይሬክተርን አነጋግረናል። በመጨረሻው ጥንቅራችን ደግሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር ዝግጅትን መነሻ አድርገን ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ዲቪዚዮን የከባድ ጥገና ማዕከል ምክትል አዛዥ ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡትን ገለፃ ወደእናንተ እናደርሳለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

12/31/25 • 60:00

“ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁን ኢኮኖሚውን በማረጋጋት እና ተጨባጭ እድገት ወደሚታይበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል … ዛሬ በሩሲያ እያየን ያለነው የኢኮኖሚ ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የፑቲንን አመራር ተጽእኖ ፈጣሪነት ነው” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አዉሮፓዉያን ዛሬም በከሸፈ የቁማር መንገዳቸው ቢቀጥሉም የሩስያ ገናና ድል ግን ቀጥሏል። ”አውሮፓውያን በውጭ አገራት የተቀመጡ የሩሲያን ንብረት እና ገንዘብ በመውሰድ ለዩክሬን ለመስጠት ማሰባቸው የደቡቡ ዓለም ከአውሮፓውያን ጋር የሚኖረውን አሰራር እንዲያጤን ቀጥተኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አንዳለ ንጉሴ ናቸው።  በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዓመቱ ማጠቃለያ መግለጫ ወቅት ያነሷቸዉን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ከዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ እና ከደቡብ ለደቡብ ትብብር አንፃር የሚኖራቸዉን አንድምታዎች እንቃኛለን። ለዚህም ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉን ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋን (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩን አንዳለ ንጉሴን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

12/24/25 • 60:00

“የብሪክስ መድረክ ለአባል ሀገራት የበለጠ ስትራቴጂካዊ፣ ዘላቂ እና የጋራ ጥቅምን መሰረት ያድረጉ ግንኙነቶችን ለመመስረት እድል ይሰጣል። ከዚህ አናፃር የኢትዮጵያ እና የህንድ ግንኙነት ከዚህ ማዕቀፍ በእጅጉ ይጠቀማል” ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት ከብሪክስ አገራት ትብብር አንፃር ቀዳሚ ጉዳዩ አድርጎ ይቃኛል። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን የሶቪየት ኅብርት ለአፍሪካ የነፃነት ምን ሚና ነበራት ሲል ይጠይቃል ፣ ዛሬም ድረስ የቀጠለውን አጋርነትም በሰፊው እንዳስሳለን። “ሩሲያ በታሪኳ በሙሉ በአፍሪካ ሕዝቦች ጭቆና ውስጥ ተሳትፋ አታውቅም ካለማወቋም በላይ እራሷን በዓለም ዙሪያ ለተጨቆኑ ሕዝቦች ድምፅ እንዲሁም የትግላቸው ደጋፊ ነች” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የታሪክ ተመራማሪ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

12/16/25 • 60:00

"ብዙዎቻችን ከየት እንደመጣን ምንም ባናውቅም፣ ስደተኞች ግን አይደለንም። በእገታ የተወሰድን አፍሪቃውያን ነን። አያት ቅድመ አያቶቻችን ማንነታቸዉን ሳያውቁ ወደ መቃብር ወርደዋል። የ'ባሪያ' ልጆች መሆናችንን ብቻ ነው የተማርነው። ይህም ለሕዝባችን ብዙ ግራ መጋባት ፈጥሯል፣ የማንነት እጦትን ፈጠሯል"- ሲሉ ጸሐፊ እና የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኟ ጅኔል ሆይሌት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን፣ የአፍሪካን የቅኝ ግዛት በደልና ፍትህ እንዲሁም የካሳ ጥያቄን እናነሳለን ፡፡ ይሄው ጥያቄ በአውሮፓውያን ዘንድ ከመውያያ አጀንዳነት ለምን እንደሚገፋና ሌሎችንም ጉዳዮችን መነሻ አድርገን ጸሐፊ እና የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ጅኔል ሆይሌት ጋር በሰፊው እንወያያለን። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ አፍሪካ ከሕገ መንግሥታዊነት፣ ከዳኝነት ነፃነት ጋር በተያያዘ ያላትን ቀጣይ ትግል እና በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ዙሪያ ስላለው ሰፊ ክርክር እንመለከታለን። ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና አቶ ቸርነተት ሆርዶፋ፣ የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ዳኝነት ኮንፈረንስ አባልን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

12/10/25 • 60:00

‘‘ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሶሪያ ፣ ኢራቅና አፍጋኒስታን ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎች፣ በብሪታኒያ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ ተጀምረው የነበሩ ምርመራዎች በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት በድንገት እንዲቋረጡ ሆነዋል፡፡ ለምን ብለህ ብትጠይቃቸው ግን አሳማኝ ምክንያት አይሰጡህም፡፡ ተመሳሳይ ነገሮችን በተለያየ መንገድ የሚዳኝበት መንገድ በጣም የገዘፈ ነው፡፡’’ ሲሉ ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡የዛሬው ድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፡፡ በቀዳሚነት አፍሪካን ማጥቂያ የሆነው በዓለምአቀፉ ወንጀለኞች ፍርድቤት የሚደርስባት አድሏዊ አሰራርና በደልን እንዳስሳለን። ለዚህም የህግ ባለሙያና ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የአፍሪካ ደራሲያን እና አሳታሚዎች የአህጉሪቱ የባህልና የቋንቋ ሀብቶች ተገቢ እና እውነተኛ እውቅና ያገኙ ዘንድ በአለም አቀፍ መድረኮች ስለሚያሰሟቸው ጥሪዎች እንወያያለን ፤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ስነጽሁፍ መምህር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር)ጋር ቆይታ አድርገናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

12/3/25 • 60:00

"አፍሪካ እንደገና የተዋቀረ፣ ገለልተኛ፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት ዓለም አቀፍ ስረዐት ያስፈልጋታል። የተባበሩት መንግስታት አሁን ባለው አቋም የአፍሪካን ጥቅም የሚያስከብር አይደለም። በእኔ እይታ የተባበሩት መንግስታት፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚጋለብ፣ምዕራባውያን የሚነዱት ፈረስ ነው።" - ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አቶ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ጥንቅራችን ፣ በቀዳሚነት አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋመት ውስጥ ፍትሃዊ እና እኩል ውክልና ለማግኘት የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ጥረት እንፈትሻለን። ለዚህም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እን አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ የሂኑትም አቶ ዳዊት መዝገበን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችንም ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶችን ጠብቆ ማቆየት ለአፍሪካ፣ ብሎም ኢትዮጵያ እንደ ሩሲያ ካሉ አገራት ጋር ለሚኖራት መልካም ግንኙነት ስለሚኖራቸው ቦታ ደግሞ ሁለተኛው ጥንቅራችን ያስቀኛናል። በዚህ ጉዳይ ያላቸውን ሃሳብ እንዲያጋሩን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጥናት እና ምርምር ዳይሬክተር የሆኑትን መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤልን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

12/3/25 • 60:00

"እኛ ደግሞ አፍሪካውያኖች የራሳችን ታሪክ የምንነግርበት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የምናስተላልፍበት ጥበብ፣ የራሳችን መንገድ አለን። ስለዚህ ይሄ የአውሮፓ ተኮር የሆነውን አመለካከት ከአፍሪካ ስነ ጽሁፍ ውስጥ አውጥተን በአፍሪካ ተኮር ወይም ደግሞ አፍሮ ሴንትሪክ በሆነው ስንተካ አንደኛ ዲኮሎናይዝ እያደረግን ነው ማለት ነው።" ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነጽሁፍ መምህርና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ስነጽሁፍ አስተማሪ እና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰን (ዶ/ር) አነጋግሮ የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ለማላቀቅ መደረግ ያሉባቸውን ጉዳዮች በቀዳሚው ክፍል እናስደምጣችኋለን። እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ መለያ የሆኗትን አትሌቲክስ (አትሌቶቿን) እና ቡናን በዲፕሎማሲ ረገድ ''ሶፍት ዲፕሎማሲ'' አማራጭነት መጠቀም በምትችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሁለተኛው ጉዳያችን አድርገነዋል። ለዚህም የታሪክ አጥኝ እና የመገናኛ ብዙሀን ጥናት ባለሞያ የሆኑትን ተረፈ ወርቁን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

11/24/25 • 60:00

 "ይህ የአፍሪካ ዕዳ ተብሎ የሚጠራው ነገር በቀላሉ መወገድ አለበት። ሌባ ከቤትህ ሰርቆ ሲያበቃ እንዴት እንካ ቤትህን ስራበት ብሎ ገንዘብ ሊያበድርህ ይችላል? እንዴትስ ከራስህ ሰርቆ ያበደረህ ገንዘብ ላይ ወለድ ሊጥል ይችላል? ይህ ግራአጋቢ ነገር ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ተወካይ ከሆኑት አምብሮስ ኪንግ (ራስ ወልደ ስላሴ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ "ፍትህ ለአፍሪካውያን እና አፍሪካዊ ዝርያ ላላቸው ሁሉ በካሳ መልክ" የሚለው ሐሳብ የአፍሪካ ኅብረት እ.ኤ.አ 2025 መሰባሰብያ ጭብጥ ነው። የአፍሪካ ፍትህና ካሳ በምን መልኩ ሊለካ ይችላል ፣ መልሱ ከባድ አከራካሪም ነውና ለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን በአዲስ አበባ ተወካይ ከሆኑት አምብሮስ ኪንግ (ራስ ወልደ ስላሴ) ጋር ቆይታ አርጓል። የኢትዮጵያ የባህር ባለቤትነት ጥያቄን በተመለከተ በሰላሌ ዩኒቨርስቲ የታሪክና የቅርስ ጥበቃ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪውን ደረጀ ኃይሌ አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

11/19/25 • 60:00

"አፍሪካ የገንዘብ ሀብት እጥረት እንደሌለባት ልብ ማለት ያስፈልጋል - አፍሪካውያን የጎደለን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የሚሆን ፍላጎት ነው። በእውነት የሚያስፈልገን ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት የሚያስችል ቁርጠኝነት ነው። የዚህ ዓይነቱ ቁርጠኝነት ስለጎደለንም ልብ በሚሰብር መልኩ ከውጭ በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ሆነን ቀርተናል" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ድራም ኦፍ ቼንጅስ በዛሬው ዝግጅቱ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን በስፋት ይዳስሳል ፡፡ አህጉሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ቀጣናዊ ጥምረቶች ለአህጉር አቀፍ ትስስር ካስማዎች ናቸው ወይስ በውስን የፋይናንስ አቅማቸው ምክንያት አፍሪካን የማጥመጃ መረብ ሆነዋል ? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው በጆሃንስበርግ ዩኒቨርስቲ መምህርና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብ እና ውይይት ተቋም ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ እና የአስተዳደር እና የአፍሪካ ውስጥ የንግድ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ 'በአረቡ ዓለም ፖለቲካ በተሳሳተ መንገድ እንድትሳልና ብሔራዊ ጥቋንም ለማስከበር ' የአረብ ሊግ ሊሆን ቀጣይ የጥምረት መዳረሻዋ እንዴት ሊሆን እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ምክለታቸውን አጋርተውናል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

11/18/25 • 60:00

"ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሁሉ አቅፋ ይዛለች ። ስለዚህ አንድ ሰው አፍሪካን በእውነት መጎብኘት ከፈለገ፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሁሉንም ማየት ይችላል።[…] ስለዚህ፣ በብሪክስ ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አገሮችን፣ ጥሩ የህዝብ ብዛትን እና ጥሩ ኢኮኖሚን በተመሳሳይ ጊዜ እናገኛለን፤ ይህም እነርሱን የቱሪስት እንግዶቻችን ልናደርጋቸው ያስችለናል።[...] ስፑትኒክ አፍሪካ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ብዙዎች ጋር ለማድረስ ይረዳናል። ሚዲያው ቢሮውን በኢትዮጵያ መክፈቱም ከራዕያችን ጋር በእጅጉ የተጣጣመ ነው" - ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማን አነጋግሮ የኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች ሀገራት ጭምር በማዞር አዲስ የቱሪዝም የገበያ እያማተረች ስለመሆኗ ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን ይዳስሳል። እንዲሁም ቻይና በቅርቡ ለአፍሪካ ሀገራት '' እተገብረዋለሁ'' ያለችውን የዜሮ ታሪፍ ጉዳይ ያነሳል። ለዚህም የፓን አፍሪካ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ክቡር ገናን አነጋግሯል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

11/12/25 • 60:00