Show cover of Continental Drift

Continental Drift

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.

Tracks

ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በምዕራባውያን ላይ ያነሱት የሉዓላዊነት ጥያቄ የዓለምን ጂኦ-ፖለቲካ ቀይሮታል። ለዘመናት "ፀረ-ሽብር" በሚል ሽፋን የተካሄደው የሀብት ዘረፋ እና ጣልቃ ገብነት ሲያበቃ፣ ሀገራቱ ፊታቸውን ወደ ሞስኮ አዙረዋል። ለመሆኑ ይህ የሽግግር ወቅት ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት እና ለባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓት ምን ትርጉም አለው? " የሩሲያና የአፍሪካ ግንኙነት የሚወሰነው በሩሲያና በአፍሪካ መሪዎች ነው። እና ይህ መሰረታዊ ነገር ነው። የሁለቱ ማለትም ሩሲያ እንደ አንድ ሀገር፣ አፍሪካ እንደ ብዙ ሀገር—የሚሰጡት፣ መሪዎቻቸው የሚወስኑት ነገር ወደፊት የሁለቱን ግንኙነት... የሚወስን ይመስለኛል።" — ፕሮፌሰር ዘነበ ክንፉ፣ በሩሲያ የኢትዮጵያውያን ማህበር ፕሬዝዳንት እና በሩሲያ የስቴት ዱማ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አማካሪ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን (AES) ምስረታን፣ የሩሲያን የ"ያለ ጣልቃ-ገብነት" የአጋርነት መርህ እና የአፍሪካን አዲሱን የነጻነት ትግል ከፕሮፌሰር ዘነበ ክንፉ ጋር በሰፊው እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

2/4/26 • 60:00

ኢትዮጵያ የራሷን ገንዘብ ኖት በሀገር ውስጥ የደረሰችው ውሳኔ፣ ከውጭ ኩባንያዎች ጥገኝነት የመላቀቅ እና የገንዘብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ውሳኔ ከዶላር ጥገኝነት ለመውጣት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በሌላ በኩል Make Africa Borderless Now ''አሁን አፍሪካን ንብር የለሽ እናድርጋት ንቅናቄ'' አህጉሪቱን ትስስር ዕውን ለማድረግ እየሰራ ነው። "የራስን ገንዘብ ማተም ካልተቻለ ፣ በራስ ገንዘብ መበደር ፣ መገበያየት እና መቆጠብ ካልተቻለ ፤ ሉዓላዊነት እንደ ሀገር አደጋ ላይ ይወድቃል።[...] የራስን ገንዘብ ማተም የራስን ሀገር በራስ አቅም ከማስተዳደር ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው።" ሲሉ መርዕድ ፍቅረዮሐንስ፣ የፕራግማ ኢንቨስትመንት አማካሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ኢትዮጵያ ገንዘቧን በሀገር ውስጥ ማተም የመጀመር ዉጥኗን ትርጓሜ ከኢንቨስትመንት ባለሙያው መርዕድ ፍቅረዮሐንስ ጋር እንፈትሻለን።እንዲሁም አፍሪካን ለትስስር ማነቆ የሆነውን የድንበር ሀሳብን ስለሚታገለው ንቅናቄ ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ባን ዴንግ (ዶ/ር)ጋር እንወያያለን ። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

1/28/26 • 60:00

ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች ለማንቀሳቀስ ስታቅድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ የአፍሪካን የአቪዬሽን ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ የኤርፖርት ፕሮጀክት ጀምሯል። እነዚህ የአየር እና የየብስ መሰረተ ልማቶች ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና ለአፍሪካ ትስስር ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ነው፣የኢኮኖሚ ዞኖችም ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ። "ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ማዕከላዊ ሚና መጫወት አለባት። ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያን የአፍሪካ ማኑፋክቸሪንግ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል እንድትሆን ይረዱናል።[...] የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን በመጠቀም ያለንን አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር አለብን።" ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ዝግጅታችን፣የኢትዮጵያን የኢንደስትሪ ልማትና ከአህጉራዊ የነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት ተጠቃሚነት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ጋር እንመለከታለን። አዲሱ የኤርፖርት ፕሮጀክት ለአፍሪካ አቪዬሽን ያለውን ፋይዳም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ያስተላለፉትን መልእክት እንቃኛለን። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

1/22/26 • 60:00

የ'ኢትዮ-ፔይ' መጀመር ኢትዮጵያ በዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥናል። በሌላ በኩል፣ ሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ብርሃን ባልታደሉበት አፍሪካ፣ የኢነርጂ አቅርቦትንና ብቃትን ማሳደግ ወሳኝ የቤት ሥራ ሆኗል።"በዶላር ላይ ጥገኝነት አይኖርም... ቴክኖሎጂው ክፍያዎች በቀላሉ እንዲተላለፉ ያስችላል። ነገር ግን ወደ ተግባራዊ ትግበራው ስንመጣ፣ የሕግ ማዕቀፍ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል። በህግ በኩል፣ ሁለቱ ሀገራት ክፍያው እንዴት እንደሚፈጸምና የገንዘብ ምንዛሪው እንዴት እንደሚሆን መስማማት አለባቸው።" ሲሉ የኢት-ስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ዝግጅታችን፣ 'ኢትዮ-ፔይ' ስለሚፈጥረው ዕድል ከኢት-ስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ጋር እንወያያለን። ቀጥለን የአፍሪካን የኢነርጂ እንቅፋቶችን ከ'ሰስተነብል ኢነርጂ ፎር ኦል' የኢነርጂ ብቃት ባለሙያ ኤልዛቤት ዋንጌሲ ቼጌ እና ከደቡብ አፍሪካ የኤሌክትሪክ እና ኢነርጂ ምክትል ሚኒስትር ሳማንታ ግራሃም-ማሬ ጋር እንፈትሻለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

1/15/26 • 60:00

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ "ፋይዳ" ከሙከራ ደረጃ አልፎ አሁን ላይ መላውን ሀገራዊ ሥርዓት እያስተሳሰረ ይገኛል። ባንኮችና የክፍያ ሥርዓቶች ከፋይዳ ጋር መገናኘታቸው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ትልቅ ዕድል ቢሆንም፣ የዜጎች የግል መረጃ ደኅንነት ለመጠበቅ የተለያዩ ስልቶች እየተተገበሩበት ነው ። "የግል መረጃችሁ በትላልቅ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች እጅ ሆኖ በየትኛው የሕግ ሥልጣን ሥር እንደሚገኝ እንኳን ማወቅ[አይቻልም]፤ ምክንያቱም ይህ የኩባንያዎች ምስጢር ነው። ፋይዳን በሚመለከት ግን አንድ ያደረግነው መልካም ነገር የመረጃ ቅነሳ ወይም 'ዳታ ሚኒማይዜሽን' የተሰኘውን መርህ መከተል ነው ፤ ስለዚህ ስለ አንድ ሰው ብዙ መረጃዎችን አንወስድም።" ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ፋይዳ እንዴት የዲጂታል ኢኮኖሚው መሠረት እየሆነ ነው? የመረጃ ደኅንነትና ግልጽነትስ እንዴት ይረጋገጣል? የሚሉትን አንጋቢ ጉዳዮች የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ጋር በጥልቀት እንመረምራለን ።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

1/13/26 • 60:00

የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ቀጠና በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ናቸው። እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው ዕውቅና፣ የሁቲ አማጽያን ዛቻ እና ከእስራኤል ጋር የገብበት ፍጥጫ ቀጥሏል፡፡ በሌላ በኩል፣ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ከብሪታኒያ ሙዚየም "በብድር" ሳይሆን በክብር የመመለስ ትግል የአፍሪካዊያን ሌላ ሜዳ ሆኗል። "እስራኤል ለሶማሌላንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ እና አስፈላጊነት ትኩረት እየሰጠች ነው፤ ምክንያቱም ሁቲዎች በእስራኤል ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኢላማዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው። ስለዚህ ይህ አንዱ ጉዳይ ነው።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ የሶማሌላንድ የሀገርነት እውቅናና ትርጓሜውን ከፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ጋር እንፈትሻለን። ተዘርፈው ለእይታ የሚቀርቡበት የብሪታኒያ ሙዚየም ቅርሶችን "በውሰት" ለአፍሪካ ሀገራት የመስጠት እቅድና የተዘረፉ ቅርሶችን የማስመለስ ሂደት የትግል መልክን በተመለከተም ከቅርስ አስተዳደር እና ጥበቃ ከፍተኛ ተመራማሪ ተስፋዬ አራጌ ጋር እንወያያለን።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

1/2/26 • 60:00

አፍሪካ በአሁኑ ወቅት የዓለም የኃይል ሚዛን በሚቀያየርበት ባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ የራሷን ድምፅ ለማሰማት እና የፖለቲካ ተጽዕኖዋን ለማሳደግ እየጣረች ትገኛለች። "እንደሚታየው አፍሪካ እና እስያ በተለይም ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ነው። በትምህርት ረገድም ሰፊ ግንኙነት አለን። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አፍሪካ ውስጥ ከሩሲያ ትምህርትን እና ሌሎች ድጋፎችን ለማግኘት የሚያስችሉ የዳታ ማኔጅመንት ዕቅዶች አሉን።" ሲሉ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ መምህር ይመር አሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ያላትን ስልታዊ ቦታ እና ከሩሲያ ጋር ያላትን ተግባራዊ ግንኙነት በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ መምህር ከሆኑት ይመር አሊ ጋር እንፈትሻለን። በመቀጠልም፣ የአስተሳሰብ ሉዓላዊነትን እና አፍሪካዊ የሆኑ የንድፈ-ሀሳብ እውቀቶችን የማዳበር አስፈላጊነትን የ"ካፒታል ቫዮለንስ " መጽሐፍ ጸሐፊ ዋቪንያ ማካይ ጋር በጥልቀት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

12/30/25 • 60:00

የኢትዮጵያ የቅመማ ቅመም ዘርፍ ባለው ከፍተኛ እምቅ አቅም ልክ ተገቢውን ዋጋ አላገኘም። በሌላ በኩል ደግሞ አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስፈን በደቡብ-ደቡብ ትብብር እና በሩሲያ-አፍሪካ ትብብር ላይ እየሰራች ነው። የጓሮ እርሻዎች ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅድስት አምዴ "እኛ ጋር ወደ 23 የሚደርሱ የምግብ ቅመሞች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን እናውቃቸዋለን፤ አንዳንዶቹን አናውቃቸውም። ወደ 800 የሚጠጉ የመድኃኒት ዕፅዋትም አሉን። ይህ በጣም ሰፊ የልዩ ልዩ ዝርያዎች ሀብት ነው። በየቦታው አይገኝም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ዕድል አለ ብዬ አስባለሁ።" ስትል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የጉዋሮ ማይክሮ-ፋብሪካዎች የአርሶ አደሩን ገቢ እና የሀገርን የግብርና ዘርፍ መዋቅር እንዴት እየቀየሩ ነው? የሚለውን እንመለከታለን። ለዚህም የጓሮ እርሻዎች ተባባሪ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅደስት አምዴን ጋብዘናል። እንዲሁም፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ዲን ዘሪሁን ደምረው (ዶ/ር) እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በትብብር እንዴት ታረጋግጣለች? በሚለው ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት እንፈትሻለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

12/18/25 • 60:00

"[...] የብሪክስ ቁልፍ መርህ የሉዓላዊነትን ማስከበር፣ የሀገራዊ ሁኔታዎችን እና ነባራዊ እውነታዎችን ማክበር ነው። በኢነርጂ ዘርፉም ቢሆን የምናደርገው ትብብር ይህንን ያገናዘበ ነው።" ሲሉ የሩሲያ የኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካይ አናስታሲያ ሺሮኮግራድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ሶስት የተለያዩ ወሳኝ ጉዳዮችን እንመለከታለን በቀዳሚነ የብሪክስ የኢነርጂ ትብብር ለኢትዮጵያ ምን ይዞ መጥቷል ፣ ለአፍሪካ የኢነርጂ ሉዓላዊነትስ ምን ማለት ነው ስንል የሩሲያ ኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካይ አናስታሲያ ሺሮኮግራድ አነጋግረናቸዋል፡፡ በሁለተኛው ክፍል ከታህሳስ 2 እስከ 3 በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ መነሻ አድርገን አፍሪካንና የሃይል ትስስርን እንዲሁም የብሪክስ ጥምረትን ሚና ከኬንያ ኢነርጂ ሚኒስቴር የታዳሽ ኃይል ረዳት ዳይሬክተር ጆርጅ ኒዮንጋዮ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የኢነርጂ ብቃት ባለሙያ ጃሌል ቻብቹብ እና ከሌሎች የጉባዔው ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ጠይቀናል። የሀገር ውስጥ አምራቾች የገበያውን ክፍተት እንዴት እየሸፈኑ ነው? የ ቅመም ዕፅዋት ውጤቶች መስራች መቅደላዊት ያሬድ እና ዲዛይነት ቤተልሄም ጌታቸው ያነጋገንበት ጉዳይም በዚሁ መሰናዶ ውስጥ ተካትቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

12/15/25 • 60:00

አፍሪካ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለእዳ ክፍያ በማውጣት፣ ከጤናና ትምህርት በለጠ የፋይናንስ ጫና ውስጥ ወድቃለች ። " አለምዓቀፉን የገንዘብ ተቋም በተቀበልክ ጊዜ፣ የማክሮ ፖሊሲህን በሙሉ አሳልፈህ ትሰጣለህ። እኔ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ነኝ፤ ሁሉንም ፖሊሲዎች አውቃለሁ። ከአይ.ኤም.ኤፍ. ጋር ስምምነት ስትፈጽም፣ የማክሮ ፖሊሲ የመወሰን አቅምህን በጠቅላላ ታጣለህ። የፊስካል ፖሊሲ ታጣለህ፤ የገንዘብ ፖሊሲ ታጣለህ፤ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ታጣለህ። በመሠረቱ ራስን በራስ የማስተዳደር አቅምህን ታጣለህ።" ሲሉ የማክሮ ኢኮኖሚክስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ማን ነው? በሚለው ሀሳብ ዙሪያ የማክሮ ኢኮኖሚክስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡ የኢትዮጵያ የወይን ዘርፍ በአለምአቀፍ ገበያ እንዴት ተወዳዳሪ መሆን ይችላል ? የብሪክስና የደቡብ ለደቡብ ትብብሮችስ ምን አይነት እድልና አቅሞች ይፈጥሩለታል ስንል ከወይን ባለሙያ ዳዊት ዳንኤል ጋር ሰፊ ውይይትን አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

11/19/25 • 60:00

ፍትህ የውጭ ተጽዕኖን ሲከናነብ ፣ ማን ይዳኛል ? ማንስ ደግሞ በነጻ ይለቀቃል? '' የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ምስረታን ስንመለከት፣ አብዛኞቹ ለክስ የሚቀርቡ ጉዳዮች የአፍሪካ ጉዳዮች ሆነው እናገኛቸዋለን። በአህጉር አቀፍ ደረጃ ለጦርነቶች አስተዋጽኦ የሚያደርጉት አብዛኞቹ ሀገራት ግን የአፍሪካ ሀገራት አይደሉም። ስለዚህ እንደ አፍሪካውያን የዉስጥ ጉዳዮቻችንን የምናይበት የአፍሪካ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምናቋቁምበት ጊዜ አሁን እንደሆነ አምናለሁ። ራሳቸውን ከአይሲሲ ቻርተር ያገለሉትን የአፍሪካ ሀገራትንም ማድነቅ ወይም ማመስገን እወዳለሁ '' ስትል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች። በዚሁ የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን እናያለን ፣ አፍሪካዊያን ለምዕራባዊያ ባደሩ የ'ፍትህ ተቋማት ስለሚፈጸምባቸው በደልና እና የአፍሪካ ሀገራት አማራጮች ምንድን ናቸው ስንል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች የቀድሞ ተመራቂዎች ኮሚሽን ፌዴሬሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር አልፍሬድ ኤሊ ፣ የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲን እና የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን የሰሜን አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ራታኒያ ዳዊን ጠይቀናል፡፡ በሌላኛው ጉዳያችን ደግሞ የአፍሪካ የግብርናና ገጠር ልማት ጦችን ለማስመዝገብ አፍሪካ ምን ማድረግ አለባት ስንል የኢንተር አፍሪካ ፊቶሳኒተሪ ካውንስል አስተባባሪ ዶ/ር ሳሊዩ ኒያሲ፣ የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቫላካቲ እና ሌሎችንም አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

11/14/25 • 60:00

ኢትዮጵያ የብዝሃ ሀብት ባለቤት ናት ፣ ተፈጥሮ ካደላት መገለጫዎቿ እኩሌታ ብዙኃ ቋንቋና ባህል ያላት መሆኑ የልዩ መልካነቷ ማሳያ ነው፡፡ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና የሙዚቃ መሳሪያዎቿም ትናንቷን የሚዘክሩ ፣ የነገን መልክ ዛሬ ላይ ለመቅረጽ በብዙ የሚጥሩ ናቸው፡፡ እንዴት ? “ አንደኛ የስራ እድል ምንጭ ይሆናል። የሚጫወቱ ሰዎች ቢበዙ የስራ እድል ነው ብዙ ሙዚቀኛ በዚህ ሙያ ላይ ያሉ ሙዚቀኞች እንደመኖሪያቸው ይሆናል። ሁለተኛ ደግሞ የሀገር ሀብት ነው። እንደ ሀገርም መሸጥ ይቻላል ሙዚቃን መሸጥ ይቻላል ፣ በነገራችን ላይ ያው [ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንጻር] በተለያየ መንገድ ገቢ ማግኘት አለብን ብዬ አስባለሁ። እና አንደኛው ሙዚቃ ነው፡፡ ሙዚቃ በትልቁ ገቢ ማምጣት ይችላል ብዬ አስባለሁ ፤ ከሌላው አለም። ሙዚቃችንን ብንሸጠው እንደ ሀገር እንጠቀማለን። ዋናው ደግሞ የኢትዮጵያን ጥሩ ገጽታ ታስተዋውቂበታለሽ። ” ሲል የሙዚቃ አጥኚው እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያዊያንን ማንነት ለመላዉ ዓለም ስለሚያንጸባርቁ ባህላዊ ዉዝዋዜዎች እና በኢትዮጵያዊያን መገለጫ ስለሆነው ዋሽንት አንስተን ስለባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና ሁሉንአቀፍ አቅማቸው በሰፊው እንነጋገራለን ፤ ለዚህም የፈንዲቃ ባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ጋብዘናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

11/14/25 • 60:00

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ170 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከውጪ ለምታስገባው የእንጨት ዉጤቶች ወጪን ታወጣለች ።  [...]መንግሥት የእንጨት ሥራ ውጤቶች ከውጭ እንዳይገቡ ለማድረግ ወይም ቢያንስ ለመቀነስ ዉሳኔ አሳልፏል። ነገር ግን በውስጡ ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ምክንያት ይህ ውሳኔ ተሰርዟል፣ የእንጨት ውጤቶች እንደገና ለማስገባት ተፈቅዷል። ነገር ግን ክልከላው በተጣለበት አስር ወራት ጊዜ ውስጥ እንኳን በሀገር ውስጥ ገበያው ፍላጎት ምክንያት ብዙ ሀገር በቀል የእንጨት ሥራ ውጤት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በየአቅጣጫው መጥተው አይተናቸዋል።” ሲሉ የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለሀገሪቱ የፈጠራ ኢኮኖሚ ያላቸውን ሚና ፣ ፈተናና እድሎች በሰፊው እንመለከታለን፡፡ ለዚህም የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ እና የፓራዳይዝ ፋሽን ባለቤትና ዲዛይነት ገነት ከበደን ጋብዘናቸዋል፡፡ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

10/28/25 • 60:00