Show cover of African Heights Show

African Heights Show

ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

Tracks

''እንሰት በአፍሪካ ቀጣዩ ዋና ምግብ ይሆናል። በሀገራችን ትልቁ ችግር የምግብ ብዝሃነት ያንሰናል። ተፈጥሮ በሰፊው ሰጥቶናል ግን አንጠቀመውም — አንድ ሀገር ሉዓላዊ ናት የምትባለው በ ራሷን ስትጠብቅ ብቻ አይደለም በምግብ ስትችል ነው'' - ሲሉ አዲሱ ፈቃዱ አንዴታ(ዶ/ር)፣ የግብርና ሳይንቲስት፣ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ በተለይም የሀገር በቀል የምግብ ሰብል በሆነው እንሰት አቀነባበርና ማብላላት ሂደት ላይ ያተኮረ ምርምር ያካሂዱ ባለሙያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው ፕሮግራማችን የሀገር በቀል የምግብ ሰብል የሆነው እንሰት ለምግብ ዋስትናና ለተመጣጠነ ምግብ ያለውን አቅም፣ በምግብ ማቀነባበርና ማብላላት ሂደት የሚኖረውን የምርምር ሚና፣ እንዲሁም ባህላዊ የምግብ ሀብቶቻችንን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዴት የበለጠ ጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል እንዳስሳለን። ለዚህም አዲሱ ፈቃዱ አንዴታ (ዶ/ር) ፣ የግብርና ሳይንቲስት፣ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ በተለይም የሀገር በቀል የምግብ ሰብል በሆነው እንሰት አቀነባበርና ማብላላት ሂደት ላይ ያተኮረ ምርምር ያካሂዱ ባለሙያ ዕይታቸውን በሰፊው ያካፍሉናል።

11/2/26 • 120:08

''እውነተኛ ሥነ-ምግባር ከውጭ አገር ተሸክፎ የሚመጣ ሸቀጥ ሳይሆን፣ ከህዝብ ታሪክ፣ መንፈሳዊ እሴትና አኗኗር የሚቀዳ ነው። አፍሪካውያን የምዕራባውያንን ግለሰብ-ተኮር እይታ አውርደው ከመቀበል ይልቅ የራሳቸውን ማህበራዊና ባህላዊ የሞራል መሰረት ካልጠበቁ የባህል ወረራ ሰለባ ይሆናሉ::” ሲሉ የኢትዮጵያ የስነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት አባ መዝገቡ ካሳ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ: የሥነ-ምግባር ሉዓላዊነት፡ ዓለም አቀፍ እሴቶች እና የአካባቢ ማንነት በሚል ርዕስ አፍሪካ የሞራል መሰረቷን እንዴት መጠበቅ ትችላለች በሚለው ላይ እንመክራለን። አባ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮጵያ የስነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት እና የቅድስት ሥላሴ ቴዎሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር ደግሞ ዕይታቸውን ያጋሩናል።በክፍል ሁለት: የአፍሪካ ሀገራት ከውጭ ተፅዕኖ ነፃ የሆነ እና ገለልተኛ ፖሊሲን ለመከተል የሚያደርጉት ጥረት በሚል ርዕስ አህጉሪቱ ከኒዮ-ኮሎኒያሊዝም እና ከጂኦ-ፖለቲካዊ ጫናዎች ወጥታ ስትራቴጂካዊ ነፃነቷን እንዴት ማረጋገጥ እንዳለባት እንቃኛለን። አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ደግሞ ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

11/2/26 • 120:08

በ3ኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ጋር በተገናኘ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮ፣ ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ትብብር በማጠናከር ዙሪያ ያላትን አቋምና ራዕይ በግልፅ አቅርበዋል። በዚህም የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፣ የጉባኤውን ቁልፍ መልዕክቶች፣ የጂኦፖለቲካ ተፅዕኖዎችንና ለአፍሪካ የወደፊት ዕድሎች የሚኖራቸውን ትርጉም እንዳስሳለን።በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ጥናት ክፍል የፖሊሲ ጉዳዮች ተመራማሪው አበራ ሄብሶ ደግሞ ሙያዊ ዕይታቸውን አካፍለውናል። በተጨማሪም የዳሰሳችን አካል በሆነው የተባበበሩት መንግሰታት ድርጅት ማሻሻያዎች ዙሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ትዛዙ መሃመድ ሀሳቡን አጋርቶናል።

11/2/26 • 120:08

''የ3ኛው የሩሲያ አፍሪካ ሰሚት በጣም ጥሩ ሆኖ ነው ያገኘሁት፤ እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተሳተፍኩት፤ ለአፍሪካ ሀገር እንደሁም ለሩሲያ በጣም በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚ፣ በትምህርት ዙሪያ በጣም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለን ነው የምንጠብቀው — እኔም የመጣሁበት አንደኛው በምርምር ዙሪያ እንደዚሁም በትምህርት ከሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትብብር ለመፈራረም ነው - ሲሉ ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።''በዚህ ዝግጅት የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፣ የጂኦፖለቲካ ለውጦች፣ የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች፣ የኢኮኖሚ ትብብርና የሩሲያ–አፍሪካ ግንኙነት የወደፊት አቅጣጫ ላይ ጥልቅ ዳሰሳ እናደርጋለን የጉባዔው ተሳታፊዎች፣ ዶ/ር ዮናስ አዳዬ አዴቶ – የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም (IPSS) የቀድሞ ዳይሬክተር እንዲሁም፧ ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሀሳባቸውን አጋርተውናል። በክፍል ሁለት ከዶ/ር ደርጄ ጌታሁን እና ከክብሩ ቸርነት፣ የቀድሞ የሩሲያ ተማሪዎች ቆይታ ጋር አድርገናል።ሙሉ መረጃውን ይከታተሉ፡

11/2/26 • 120:08

“የቅኝ ግዛት ትምህርት ዋና ዓላማ ነፃ፣ እራሱን የቻለና ተመራማሪ ትውልድን መፍጠር ሳይሆን የቅኝ ግዛት ሀገራትን የሀብት ብዝበዛና አስተዳደር የሚያስፈጽም ታዛዥ መዋቅርን መገንባት ነበር። አፍሪካውያን ታሪካዊ ቀጣይነታቸውን እና የራሳቸውን የአስተዳደርና የእውቀት ፍልስፍና ዳግም ካላረጋገጡ በቀር፣ ከአእምሮአዊ የበታችነት ስሜትና ከፖለቲካዊ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ መላቀቅ አይችሉም።” ሲሉ የየፓን አፍሪካዊ አስተሳሰብ ትምህርት ቤት መስራች እና ዳይሬክተር ናይጄል ስቱዋርት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፡ በክፍል አንድ፦ የቅኝ ግዛት የትምህርት ሥርዓት በአፍሪካ የፖለቲካ አስተሳሰብና ማንነት ላይ ያሳደረውን ዘላቂ አሉታዊ ተፅዕኖ፣ የሀገር ውስጥ እውቀቶችንና ታሪክን ወደ ትምህርት ገበታ በመመለስ አእምሮአዊ ነፃነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ እና የዲጂታል መድረኮችን ሚና ከፓን-አፍሪካኒስቱ ምሁር ከናይጄል ስቱዋርት ጋር በጥልቀት እንዳስሰዋለን። በክፍል ሁለት፦ በሳህል ቀጠና ሀገራት (ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር) የፈረንሳይ የነዮ-ኮሎኒያል የበላይነት መዋቅር (Françafrique) ስረ-መሰረታዊ መፍረስ፣ የሴኤፍኤ ፍራንክ (CFA Franc) የገንዘብ ጥገኝነት፣ የሳህል ሀገራት ህብረት (AES) ምስረታ እና ቀጠናው ወደ አዲሱ የጂኦ-ፖለቲካዊና የባለብዙ ወገን (Multipolar) አለም አቀፍ ትስስር የሚያደርገውን ሽግግር ከፖለቲካና ኤኮኖሚ ተንታኙ ከካባላ ጆን ጋር ቃኝተነዋል።ሙሉውን መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡ 

10/21/26 • 120:08

“በአፍሪካ ያሉ አብዛኛዎቹ ሀገራት እና ህዝቦች ስለ ሩሲያ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ፤ የሩሲያን አቋምም በተሻለ ሁኔታ መረዳት ይሻሉ። እነሱም አብረዋቸው ሁለቱም ወገን በሚጠቀሙበት የትብብር ስርአት መስራት የሚችል አዋጭ አጋር እየፈለጉ ነው፤ ሩሲያም ለእዚህ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነች።” ሲሉ በአዲስ አበባ የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን ማዕከል) ዳይሬክተር ቭላዲሚር ቭላዲሚሮቪች ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፡ በክፍል አንድ፦ የሩሲያ እና ኢትዮጵያን ታሪካዊ፣ መንፈሳዊ እና ባህላዊ ዲፕሎማሲ፣ የትምህርት እድሎችን ፣ የፑሽኪን ማዕከልን ዘመናዊ ሚና እና የሩሲያ የባህል ዲፕሎማሲ በአፍሪካ አህጉር እየሰፋ ያለበትን ስትራቴጂካዊ ሁኔታ ከማዕከሉ ዳይሬክተር ከቭላዲሚር ቭላዲሚሮቪች ጋር በጥልቀት እንዳስሰዋለን። በክፍል ሁለት፦ የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እና የክትባት ምርትን በሀገር ውስጥ መጀመር የሚጠይቀውን አህጉራዊ ጥረት፣ የአለም አቀፍ አቅርቦት ሰንሰለት ተጋላጭነቶችን፣ ለሀገር ውስጥ ማኑፋክቸሪንግ የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ፣ የመሰረተ ልማት፣ የፖሊሲ እና የፋይናንስ ማዕቀፎችን ከአለርት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት ሐኪም እና የሕፃናት ተላላፊ በሽታዎች ሰብ-ስፔሻሊስት ከሆኑት ከዶ/ር ጡረኛ አሰፋ ስዩም ጋር በስፋት ቃኝተነዋል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

10/21/26 • 120:08

መጪው ሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ፣ ከጥቅምት 28–29 ቀን 2026 በሞስኮ በሚካሄደው ውይይት በርካታ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ያደርጋል። ሀገራት የአፍሪካ አገራት ለዓለም አቀፍ የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀት ያላቸው ድርሻ አነስተኛ ቢሆንም፣ ለከባድ የአየር ንብረት ተፅዕኖዎች የተጋለጡ ሲሆኑ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስና ተመጣጣኝ የንጹህ ቴክኖሎጂ ተደራሽነትም ተግዳሮት ሆኖባቸዋል። ጉባኤው ሩሲያና የአፍሪካ አገራት በታዳሽ ኃይል፣ በአየር ንብረት ለውጥ መላመድ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በአቅም ግንባታ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እድል ይፈጥራል።''በአየር ንብረት ቀውስ ጉዳይ የበለፀጉ ሀገራት ለተጎጂ ታዳጊ ሀገራት ድጋፎ ማድረግ ይኖርባቸዋል። አፍሪካ አያደገች ያለችና ተስፋ ያላት አህጉር ነች'' ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው ፕሮግራማችን የአየር ንብረት ፍትህ፡ ሩሲያ የአፍሪካን ፍትሃዊ የአየር ንብረት ፋይናንስ እና ንጹህ ቴክኖሎጂ የማግኘት ጥያቄዎችን መደገፍ በምትችልባቸው ሁኔታዎች በተለይም ጉዳዩን ከሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ ጋር በማያያዝ ሰፋ ያለ ዳሰሳ እናደርጋለን። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ደግሞ ሙያዊ ዕይታቸውን ያካፍሉናል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

10/21/26 • 120:08

በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ (African Heights) ዝግጅታችን፦ · የሲኒማና የትርክት የበላይነትን ማፍረስ፦ በምዕራባውያን ፊልሞች የግጭት እና የድህነት መንደር ተደርጋ በአሉታዊ ገፅታ የምትሳለውን አፍሪካ ዳግም በአዲስ መልክ መገንባት ስለሚቻልበት አቅም፤  · የBRICS+ እና የሁለትዮሽ የፊልም ስምምነቶች፦ ኢትዮጵያ በBRICS የፊልም ፌስቲቫል ላይ የሚኖራት የባህል ዲፕሎማሲ ተፅዕኖ እና ድንበር ተሻጋሪ የፊልም  ትብብር  ስምምነቶች (Co-production treaties) ለሀገር ውስጥ ፊልም ሰሪዎች የሚያስገኝላቸው የፋይናንስና የገበያ ዕድሎች፤ ከኤፍሬም  ለማ  በላይነህ ጋር  በጥልቀትና  በስፋት ተመልክተነዋል።

10/19/26 • 120:08

ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦በክፍል አንድ፦"ከእግራችን ስር ያለው የተሰወረ ህይወት" በሚል ርዕስ የአፈር ብዝሃ-ህይወት ለምግብ ዋስትና ያለውን ወሳኝ ሚና፣ የኬሚካል ማዳበሪያዎች አጠቃቀምን እና የኦርጋኒክ አፈር እንክብካቤን ከሳይንሳዊ መረጃዎች ጋር እንዳስሳለን። ዶ/ር አለሙ ሌላጎ ዕይታቸውን እና ሙያዊትንተናቸውን ያጋሩናል።በክፍል ሶስት፦"አገራዊ የጤና ክፍተቶችን በተስማሚ ቴክኖሎጂዎች መፍትሄ መስጠት" በሚለው ርዕሳችን ደግሞ ውድ የውጭ ቴክኖሎጂዎችን ከመጠበቅ ይልቅ ከአካባቢ ሁኔታ ጋር የተጣጣሙ (Appropriate Technologies) መፍትሄዎችን ማሰራጨት ስላለው ፋይዳ እንነጋገራለን። ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው፣ በዘርፉ ረጅም ልምድ ያላቸው ተመራማሪ ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።

10/19/26 • 120:08

"በአዲሱ የዓለም የኃይል ሚዛን ውስጥ አፍሪካ የራሷን ድምፅና ሉዓላዊ ጥቅም ለማስከበር በሞስኮ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የተበታተነ ሳይሆን የጋራ እና የተቀናጀ አህጉራዊ አቋም ይዛ መቅረብ አለባት።"ሲሉ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት መምህር አዲስ አለማየሁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፦· ዲፕሎማሲያዊ ትብብርና የዓለም አቀፍ አስተዳደር ተጽዕኖ፦ በብሪክስ  መስፋፋትና በባለብዙ ወገን  የዓለም አቀፍ አወቃቀር ውስጥ የሩሲያና የአፍሪካ አገራት የፖለቲካ ነፃነት፣ የሉዓላዊነት መከበር እና አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ የሚገባትን ውክልና ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶች፤· ኢኮኖሚ፣ የኢንዱስትሪ ልማትና የኃይል ደኅንነት፦ የትብብር ስምምነቶችን ከጥሬ ዕቃ ንግድ ወደ ተጨባጭ የኢንዱስትሪ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግር የመቀየር ዕድሎች፤ እንዲሁም በሰላማዊ የኑክሌርና የታዳሽ ኃይል ልማት የአህጉሪቱን የኢነርጂ ነፃነት የማረጋገጥ ፋይዳ፤· የደኅንነት፣ የቴክኖሎጂና የወደፊት ስትራቴጂክ አቅጣጫ፦ የአፍሪካን የራስ መከላከያ አቅም የሚያጠናክር የጸጥታ ትብብር፣ በተጨማሪም ከ2026ቱ የሞስኮ ጉባኤ በኋላ የረጅም ጊዜ ተቋማዊና የተጠያቂነት አሠራሮችን የመዘርጋት አስፈላጊነት፤ከአዲስ አለማየሁ ጋር በጥልቀትና በስፋት ዳሰነዋል።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ!

10/16/26 • 118:56

"ሁሉም [የአፍሪካ] ሀገራት የየራሳቸው ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም፤ ዋና ዋና ፍላጎቶቻቸውን በጋራ በማጣመር እንደ አህጉር መቅረብ ቢችሉ ለሁለቱም ወገን [ለሩሲያም ለአፍሪካ ሀገራትም] ጠቃሚ እና ውጤታማ ይሆናል ብዬ አስባለው፡፡" ሲሉ በፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪጀማል መሀመድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡3ተኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ አእ.ኤ.አ ከጥቅምት 28 አእስከ 29 2026 በሞስኮ ይካሄዳል በዚህ የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅት ይህንኑ መነሻ አድርገን የሩሲያና አፍሪካ ግንኙነት በጂኦፖለቲካዊ ትስስር፣በብሪክስ መስፋፋት፣ በምግብና ኃይል ዋስትና፣ እንዲሁም በማዕቀብ ጊዜ የገንዘብ ዝውውር መፍትሔዎች እና በሁሉም አሸናፊነት ስትራቴጂ በፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሀመድ (ዶ/ር)ጋር በጥልቀት ተወያይተናል ።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡or a

10/15/26 • 120:08

በዛሬው ፕሮግራማችን ክፍል አንድ ብሔራዊ ልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ከዓለም አቀፍ የባንኪንግ ልምዶች እንዴት ማዛመድ ይቻላል፣ ደግሞስ በዘርፉ ያሉ መልካም ዕድሎችንና ተግዳሮቾችን እንቃኛለን። አስቻለሁ ታምሩ፣ በባንኪንግ ዘርፍ በተለይም በብራንዲንግ፣ ማርኬቲንግ የረጅም ዓመታት ልምድ ያላቸው ባለሙያ እንዲሁም ፍቃድ ያላቸው አማካሪ እና አሰልጣኝ ዕይታቸውን ያጋሩናል።በክፍል ሁለት ደግሞ የማዕድን ሀብት ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገት ማበረታቻ ያለው ሚናን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የጂኦሳይንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በቀለ አየለ(ዶ/ር) ያስረዱናል።

10/15/26 • 120:08

በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም የአፍሪካ አትሌቲክስ ኃያልነት መሠረት በማድረግ ከዓለም ክብረወሰኖች እስከ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ድረስ፣ ከስፖርተኞች የቪዛ እገዳ እስከ ድርብ መሥፈርት (Double standard) ያሉ ጉዳዮችን እንዳስሳለን።ለዚህም እንግዳችን ታሪኩ ተመቸ፣ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌቲክስ አሰልጣኝናተባባሪ ተመራማሪ ደግሞ ሙያዊ ዕይታቸውን ያጋሩናል።    

10/13/26 • 120:08

“የፓን-አፍሪካን የክፍያና ሴትልመንት ሥርዓት አህጉራዊ የንግድ ትስስርን ለማፋጠን የተዘረጋ ግዙፍ የፋይናንስ መሠረተ-ልማት ነው። ነገር ግን ባንኮች ጉዳዩን የቴክኖሎጂ ማገናኘት ፕሮጀክት አድርገው ብቻ የመመልከት ስህተት ይፈጽማሉ። […]ባንኮች ቀጣይነት ካለው የሳይበር ደህንነት እና የጽናት ዝግጁነት ባሻገር የታመነ የዲጂታል ባንክ ሥርዓት መገንባት አለባቸው።” ሲሉ የአይቲ ኦዲትና ዲጂታል ጎቨርናንስ ባለሙያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ኦዲት ማህበር (EISAA) ቦርድ ሰብሳቢ አቶ እስክንድር መስፍን ቸርነት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፡ በክፍል አንድ፡ የፓን-አፍሪካን የክፍያና ሴትልመንት ሥርዓት አህጉራዊ የንግድ እና የፋይናንስ ትስስርን ለማፋጠን ያለውን ሚና፣ ባንኮች በቅጽበታዊ ክፍያዎች ዘመን ሊኖራቸው የሚገባውን የሳይበር ደህንነት፣ የመረጃ ጥበቃ እና የጽናት ዝግጁነት ከባለሙያው ከእስክንድር መስፍን ጋር በጥልቀት እንዳስሰዋለን፤ በክፍል ሁለት፡ አፍሪካ አህጉር የተፈጥሮ ሀብት ጥገኝነትን በመቀነስ፣ ወጣቱን የሕዝብ ቁጥር ፣ ትምህርትን፣ ቴክኖሎጂንና የሰው ኃይል ልማትን እንደ መሠረት በመጠቀም እንዴት ጠንካራና ዘላቂ የምጣኔ ሐብት እድገትን መገንባት እንደምትችል በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሌ (ዶ/ር ) እይታቸውን አጋርተውናል፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

10/13/26 • 120:08

''የሰው ሰራሽ አስተውህሎት አስማት አይደለም። ኃይሉ የሚወሰነው በመረጃው ጥራትና በመረጃው መገኘት ላይ ነው። ቴክኖሎጂ በቀላሉ የሚታዘዝ ነገር ብቻ መሆን የለበትም፤ የሠው ሰራሽ አሰተውህሎትም ሆነ ሌላ የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ከእውነታችንና ከአካባቢያችን ጋር ማጣጣም አለብን — ሰው ሰራሽ ብዙ ሀብት የሚፈልግ ቴክኖሎጂ ነው፤ ስለዚህ በትንሹ መጀመር እና አሁን መንቀሳቀስ አለብን። የሁሉንም ሰው ሕይወት እየነካ ነው'' ሲሉ ዮናስ ገብረሚካኤል ድፈር፣ የባዮ እና አመርጂንግ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የኮምፒዩቲሽናል ሳይንስ እና የመረጃ ስርዓት ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዓለም አቀፍ የትራንስ-አትላንቲክ የባሪያ ንግድ አውድን ስንዳስስ ዛንዲሲዌ ራዴቤ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ዲፓርትመንት የዶክትሬት ተማሪ ሀሳቡን ያጋሩናል።በክፍል ሁለት የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ እውቀት (AI)፣ ቴክኖሎጂን እንደገና መቅረጽ እና ፈጠራን ማስፋፋት በተመለከተ ዮናስ ገብረሚካኤል ድፈር በባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮምፒውቴሽናል ሳይንስ እና የኢንተለጀንስ ሲስተምስ ዳይሬክተር ደግሞ ሙያዊ ዕይታውን ያጋራናል።በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበው ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ፡

10/9/26 • 120:08

ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሀይትስ ዝግጅት፡-በክፍል አንድ  ሕይወትን እንደገና መገንባት — የሴት ልጆች ግርዛት በአፍሪካ የሚያስከትለው የሕክምናና የሰብዓዊ ዋጋን እንወያያለን። ዶ/ር ቡለንት ቺሃንቲሙር፣ ዝነኛው የፕላስቲክ እና የመልሶ ህክምና ቀዶ ሐኪም ደግሞ ሙያው ትንታኔ ያጋሩናል።በክፍል ሁለት የአፍሪካ ወጣቶችን ማብቃት — የነገ መሪዎችን ስለመገንባት ዳሰሳ ስናደርግ ከናይሮቢ ኬንያ፣ የአመራር ባለሙያው ጄሚ ማክአፖሎ  ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።

10/8/26 • 120:08

ከፖለቲካዊ ነፃነት የሚሻገረው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል "ሉዓላዊነት ሁለት ዓይነት ነው፤ የውስጥና የውጭ የሚባሉ። የቀድሞ ቅኝ ገዢዎችን መንገድ ብቻ ተከትለን የምንሄድ ከሆነ፣ ለአፍሪካ ሀገራት ችግር ነው የሚሆነው - የፈፀሟቸውም ድርጊቶች ተገቢ አይደሉም በዚህም ታዳጊ ሀገራት ለሉዓላዊነታቸው መታገለል ይኖርባቸዋል።'' ሲሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አሌክሳንደር ሃይማኖት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ሁለት ዐበይት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦ በክፍል አንድ፦ “የአፍሪካ ከቀደሙት ቅኝ ገዢዎቿ ሙሉ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገው ትግል አስፈላጊነት”  ከራያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አሌክሳንደር ሃይማኖት (ዶ/ር) ጋር የተወያየንበት ሲሆን፤ በክፍል ሁለት፦ “የኑክሌር ኤነርጂ ትብብር በብሪክስ ሀገራት መካከል” በሚለው አህጉራዊ አጀንዳ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ታዋቂ ተመራማሪ ጌታቸው አዳም ወርቅነህ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንቃኘዋለን።    ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

10/6/26 • 120:08

“ብዙ ጊዜ የምናየው በሌሎች ነባር ተቋማት ስናይ ከአፍሪካ ጋር ያላቸው ግኑኝነት ለእነሱ ባደላ መልኩ ነው፡፡ ይህንን ማግኘት ከፈለግክ እነኚህን እነኚህን ነገሮች አሳልፈህ ስጥ የሚል እጅ የመጠምዘዝ ነገሮች ናቸው የሚታዩ የነበሩት። የሩሲያን አካሄድ ስንመለከተው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በመነጋገር እና መጨረሻ ላይ በተስማሙባቸው ኤሪያዎች ላይ አብሮ የመስራት እና አብሮ የማደግ ግንኙነቶችን የሚያራምድ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው የያዙት ሩሲያውያን።” ሲሉ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስዮሎጂ ት/ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የታሪክ ተመራማሪና ተንታኝ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ሁለት አበይት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦ በክፍል አንድ፦ “የፑቲን ንግግር እና የሩሲያ ከአፍሪካ ጋር አብሮ የማደግ ፍላጎት” በሚል ርዕስ፣ የሞስኮ አዲስ የጂኦፖለቲካዊ ትስስር ጥሪ፣ የባለብዙ ዋልታ እይታ፣ የታሪክ ወዳጅነት እና ለአህጉሪቱ እድገት የሚያበረክተው አወንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ ከዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) ጋር በሰፊው እንዳስሳለን።በክፍል ሁለት፦ “የመንግስታት፣ የግል ባለሀብቶች እና የማህበረሰቡ ሚና በምግብ ዋስትና እና ስነ-ምግብ” በሚለው አህጉራዊ አጀንዳ፣ አፍሪካ ሀብቷን ተጥቅማ በምግብ እና በስነ-ምግብ ራስን ለመቻል የሶስቱ አካላት ቅንጅታዊ ሃላፊነት፣ ተጨባጭ የታሪክ ምሳሌዎች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስነ -ምግብ ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር እና ተመራማሪ አዲሱ ፈቃዱ (ዶ/ር)ጋር በጥልቀት እንቃኘዋለን።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

10/6/26 • 120:08

ሁለት አበይት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦በክፍል አንድ፦ “የአፍሪካ ጥንታዊ መንግስታትን ዳግም ማገናኘት፦ ባህል፣ የኃይል ሚዛን እና ልማት ከቅኝ ግዛት ድንበሮች ባሻገር” በሚል ርዕስ፣ የአፍሪካ ባህላዊ ተቋማት ለአህጉራዊ አንድነት፣ ለሰላም ግንባታ እና ለድንበር ተሻጋሪ የኢኮኖሚ ትስስር ያላቸውን ያልተነካ አቅም ከቴተንጎል ክፕሌማኒ  እንዳስሳለን።በክፍል ሁለት፦ “ካሳ ለአፍሪካ፦ የታሪክ ተጠያቂነት እና የፋይናንስ መዋቅር ለውጥ” በሚለው አህጉራዊ አጀንዳ፣ የቅኝ ግዛት ታሪካዊ በደሎችን እና የተዘረፉ ቅርሶች ማስመለስን በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ከሆኑት ከዳዊት መዝገበ ጋር እንቃኘዋለን።

10/3/26 • 117:17

“የሆሊውድ ተጽእኖ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው፤ ጉዳቱ ያመዝናል ግን ቢሆንም ጠቃሚነቱም ደግሞ የሚካድ አይደለም። [...] ምዕራባውያን በአብዛኛው ፊልሞቻቸው ላይ የበላይነታቸውን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ […] በተቃራኒው ደግሞ የአፍሪካን ኋላቀርነት እና አስከፊ ገጽታ ለመገንባት ይሞክራሉ፤ ይህም ትውልዱ ራሱን እና ሀገሩን የሚያይበትን መንገድ የተበላሸ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡” ሲል አርቲስት ቢኒያም ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ፣ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ግጭት ጉዳዮች ተመራማሪ እና መምህር አሌክሳንደር ኃይማኖት(ዶ/ር) አፍሪካ ከጥሬ እቃ አቅራቢነት እሴትን ወደ መጨመር እንዴት ልትሸጋገር እንደምትችል ሀሳባቸውን የሚያጋሩን ሲሆን፤  በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የፊልም እና ቲያትር ባለሙያ ከሆነው ከአርቲስት ቢኒያም ወርቁ ጋር በመሆን የምእራብያውያን የፊልም እና ሌሎች የጥበብ ስራዎች ቀሪውን ዓለም የሚቃኙበት እና የሚያቀርቡበት መንገድ እንዴት ባለ መልኩ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንዳለ፣ አፍሪካ እና አፍሪካውያን ስለእራሳቸው ስላላቸው አመለካከት ላይ በተለይ የሆሊውድ የፊልም ኢንደስትሪ ያደረሰው አሉታዊ ጫና እንዲሁም የአፍሪካ እንዲሁም የኢትዮጵያ የስነጥበብ ባለሙያዎች ይህን የባህል ወረራ እንዴት ባለ መልኩ መመከት እንደሚችሉ በሰፊው ቃኝተነዋል፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

9/30/26 • 120:08

''ታላላቅ ሳይንቲስቶቻቸውን ብታይ ከእነ ኢቫን ፓብሎቭ ጀምሮ ሌሎቹን ጨምሮ ትልቅ አስተዋፅዖ ያደረገ ሀገር ነው። ግን ምዕራቡ የሚከተለውን እሳቤ ማሳየት ስለሚፈለግ ያንን ነገር ለማሳነስ ይሞክራል'' - ሲሉ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ተማሪ  ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ መሠኗዳችን በክፍል አንድ በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ እና በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎቸ መካከል በቋንቋ እና ባህል ረገድ ስለተመሰረተው ግኑኝነት በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በዩኒቨርሲቲው ስር ያለው የአለቃ ገብረሃና የባህል ጥናት እና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መሰረት ወርቁ ጋር ቆይታ ያደረግን ሲሆን፤  በክፍል ሁለት ደግሞ ሩሲያ በአፍሪካውያን ዓይን ምን ትመስላለች? የምዕራባውያን መገናኛ በዙሃን ያዛቡትን የሩሲያ ምስል እንዴት መቀየር ይቻላል በሚለው ጉዳይ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ተማሪ  ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ሃሳባቸውን አካፍለውናል፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

9/30/26 • 120:08

''የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመጠበቅ ሂደት ቅድሚያ ኃላፊነቱን ለአካባቢው ማኅበረሰብ መሥጠት ተገቢ ነው — ብዙ እንግዶች ከራሺያ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ አውቃለሁ። እንደ ክፍተት የማየው ነገር የራሺያኛ ቋንቋ የሚናገሩ አስጎብኚዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው አነስተኛ ነው  ... በእንግሊዘኛ ለማስጎብኘት እንደሚገደዱ አውቃለሁ። ምናልባቱ ይህ ትንሽ ሊያስቸግራቸው ይችላል'' ሲሉ የቱሪዝም ባለሙያ ታከሌ ኛሜ ከአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል።በዛሬው የአፍሪካ ሃይትስ ፕሮግራም ሁለት ወቅታዊና ተመጋጋቢ የቱሪዝምና የባህል ጉዳዮችን እንዳስሳለን። በክፍል አንድ፣ የኢትዮጵያን የቱሪዝም አቅም፣ በዘርፉ ያሉ እድሎች እና ሀገራችን ከዚህ ዘርፍ ሊያገኘችው የሚገባውን ጥቅም እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል እንቃኛለን። በክፍል ሁለት ደግሞ የመስከረም ወር የባህል ድምቀቶችን፣ በተለይም የመስቀል በዓልን፣ ባህላዊ እሴቱን እና ለቱሪዝም ዘርፉ ያለውን ፋይዳ እንዳስሳለን።የቱሪዝም ባለሙያዉ ታከሌ ኛሜ በሁለቱም ክፍሎች በመሳተፍ፣ በቱሪዝም ዘርፉ ያሉ እድሎችን እንዲሁም የመስቀልና የመስከረም ወር የባህል ድምቀቶችን በተመለከተ ያላቸውን ሀሳብና ዕይታ ያካፍለናል።

9/30/26 • 120:08

"ራሴን እንደ ምሁር ሳይሆን በህብረተሰቡ ውስጥ እንደ ተማሪ አድርጌ ባስቀመጥኩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ በቋንቋዎቻችን ውስጥ ያለውን ጥልቅ የፍልስፍና ይዘት ይበልጥ ለመረዳት ችያለሁ።[…]ሰዎች ባሉበት ሁሉ አስተሳሰብ አለ፤ አስተሳሰብ ባለበት ሁሉ እውቀት አለ፤ እውቀት ባለበት ሁሉ ደግሞ ፍልስፍና አለ፡፡” ሲሉ ደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር ሻባላኒ ኖኩቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ መሠኗዳችን በክፍል አንድ አፍሪካ የዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነቷን የተቀናጀ እና የጋራ በማድረግ የውጪ ጣልቃ ገብነትን እንዴት መመከት ይቻላል በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ የዓለም አቀፍ ቢዝነስ አማካሪ ከሆኑት ዙበሪ ሊጂያና የተወያየን ሲሆን፤  በክፍል ሁለት ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ መምህርት ፕ/ር ሻባናኒ ኖኩቱላ ጋር አፍሪካ የፖለቲካ ነፃነት ብታገኝም፣ ብዙ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም የአፍሪካን ታሪክ፣ ቋንቋዎች እና የእውቀት ሥርዓቶች ወደ ጎን በሚገፉ የቅኝ ግዛት ዘመን መዋቅሮች ውስጥ እየሰሩ ስለሚገኙበት ምክንያት፣ እነዚህ ውርሶች እንዴት እንደቀጠሉ እና መቀየር ስለሚቻልባቸው መንገዶች እንወያያለን፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

9/30/26 • 120:08

''ከጥሬ እቃ በተያያዘ፣ ጥሬን ወደውጭ ልኮ መልሶ በውድ ዋጋ መቀበሕ ጤነኛ ዓዕምሮ የሚቀበለው ነገር አይደለም። የአፍሪካ ባለሃብቶች ባህሪያታቸውን መቀየር ይኖርባቸዋል። አነስተኛ ቢዝነስ ላይ ስለሆነ በብዛት ትኩረት የሚያደርጉት እሱ ራሱ መሻሻል ይኖርበታል። በማዕድን ዘርፍ አፍሪካ ያላትን የመደራደር አቅም ባለሃብቶቹ በራሳቸው ማየት ይኖርባቸል - ሲሉ ዶ/ር መሀመድ ኢብራሂም፣ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር እና የማህበረ-ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ ለስፑትኒክ አፍራካ ተናግረዋል።''ሁለት ወሳኝ አፍሪካዊ ጉዳዮችን በሚዳስሰው የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ አፍሪካ ያላትን ወሳኝ ማዕድናት ሀብት እና ማዕድናቱን በአገር ውስጥ እሴት ጨምሮ የማቀናበር እድሎችና ተግዳሮቶችን እንቃኛለን።በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር እና የማህበረ-ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ  ዶ/ር መሀመድ ኢብራሂም  በዚህ ዙሪያ ያላቸውን ዕይታና ትንታኔ ያካፍሉናል። በክፍል ሁለት ደግሞ የጤና ሉዓላዊነትን፣ በጤና ዘርፉ የሚካሄደውን ሽግግር እና ይህ ለአፍሪካ በአህጉራዊ ደረጃ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ እንዳስሳለን። በቂሊንጦ ስፔሻል ኢኮኖሚክ ዞን የኢንቨስተሮች ማኅበር ፕሬዝዳንት ተሾመ በየነ ስለጉዳዩ ያላቸውን ሀሳብና ልምድ ያካፍሉናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡ 

9/30/26 • 120:08

''አሁን ባለንበት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘመን መሠታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ ላይ ወይም በማቅረብ ሂደት ላይ ነው ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያለችው'' ሲሉ የዲጂታል ሽግግርና ቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እስክንድር መስፍን ቸርነት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ሁለት ወቅታዊና ወሳኝ ጉዳዮችን በሚዳስሰው የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እድገት ለኢትዮጵያ የሚያቀርባቸውን መልካሜ ዕድሎች፣ እንዲሁም በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን እንቃኛለን። የዲጂታል ሽግግርና ቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እስክንድር መስፍን ቸርነት በዚህ ዙሪያ ያለውን ዕይታና ትንታኔ ያካፍሉናል። አፍሪካ ወሳኝ ማዕድናት ያላቸውን ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ፣ ማዕድናትን በአገር ውስጥ እሴት ጨምሮ የማቀናበር እድሎችና በዘርፉ ስላሉ ጉዳዮችም ዳሰሳ አድርገናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡ 

9/30/26 • 120:08

''ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የታዳሽ ኃይል ኃብት አላት። ለምሳሌ የፀሃይ ኃይል በኢትዮጵያ በአንድ ሜትር ስኩዌር ከ5.5 - 5.8 ኪሎዋት በአንድ ቀን ውስጥ ኃይል አለ። — ለሃይድሮ ፓወር በቢሊዮን ዶላር ነው የምናወጣው። ወደ ፀሃይ ኃይል ብንለውጠው እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ገንዘብ መስራት እንችላለን '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር  ንዋይመድኅን አበራ (ዶ/ር) ከአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።በዛሬው የአፍሪካ ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ አረንጓዴው የኢንዱስትሪ ዐቢዮትን መሠረት በማድረግ ንጹህ ኃይል የኢትዮጵያን የማምረቻ ዘርፍ ሊለውጥ ስለሚችልበት ሁኔታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ንዋይመድኅን አበራ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ይኖረናል።በኢትዮጵያና በአፍሪካ ዲጂታል አስተዳደርና ሽግግር በተመለከተ ከቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለሙያው ብሩክ ከበደ ጋር ያደረገነው ቆይታ የፕሮግራሙ ሌላኛው አካል ነው። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡ 

9/30/26 • 120:08

''የአመራርነት ቦታ ላይ ሁለት መነሳሳቶች አሉ፣ ውስጣዊ እና ውጫዊ የምንላቸው ናቸው። በዚህ መሠረት ውስጣዊው መነሳሳት ፈጠራ ሲሆን ውጫዊው ደግሞ ፋይናንስ ነው — በኢትዮጵያ በዘርፉ ሁሉም አካላት እስካሉ ድረስ የንፁህ ኃይል አቅምን በትብብር ለማሳደግ ለመንግስት ቀላል ይሆናል'' ሲሉ የታዳሽ ሃይል ዘርፍ አማካሪ ቤካ መገርሳ ለስፑትኒክ አፍረካ ተናግረዋል።''ሁለት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የመንግስና የግል ዘርፉ የንጹህ ኃይል ልማትን ለማስፋፋት ያለውን ፋይዳ እንዳስሳለን።የታዳሽ ሃይል ዘርፍ አማካሪ ቤካ መገርሳ ዕይታቸውን ያጋሩናል። በክፍል ሁለት ዕዳ እንደ መሣሪያ በሚል የአፍሪካ የፋይናንስ ጥገኝነትን እና ሁነኛ መፍትሔዎቹን እንቃኛለን። የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና 'ዲቨሎፒንግ አፍሪካ ኔው ሆራይዘንስ ዊዝ አፍሮሴንትሪሲቲ' መጽሐፍ ደራሲ ሌሄሳ ሞሎይ(ዶ/ር) ደግሞ ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ፡ 

9/30/26 • 120:08

''የአፍሪካ መሪዎች አህጉሪቷ በዓለም አቀፍ መድረክ በሚገባት ልክ አለመወከሏን መግለፃቸው ይታወቃል። አፍሪካወዊያን በራሳቸው መንገድ፣  በራሳቸው ጥረት አህጉሪቱን ከፍ ባለ ደረጃ ሊያሳድግ የሚችል ሥራ መሥራት አለባቸው። ከሌሎች ጋር ባለቸው መሥተጋብር ሊያጠናክሩ የሚችሉት በሚኖራቸው ተሳትፎ ነው- ሲሉ ደረጄ መለስ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ከአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።''ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ  አፍሪካ፣ አንድ ድምፅ፦ አፍሪካ በአንድነትና በጽኑ አቋም የበለጠ ተፅዕኖ ያለው ድምፅ የምታሰማበት ጊዜ አሁን ነው በሚል ጉዳይ እንወያያለን።ደረጄ መለስ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ዕይታቸውን ያጋሩናል።በክፍል ሁለት የቀይ ባሕር አዲሱ የኃይል ሚዛን እና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያለው ስጋት በተመለከተ እንዳስሳለን። ሰላም ታደሰ፣ በደኅንነት ጥናት ተቋም፣ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እና የቀይ ባህር ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ምልከታቸውን ያካፍሉናል።

9/30/26 • 120:08

“የአየር ሁኔታ ትንበያን ከሳይንቲስቶች ቢሮ አውጥተን በገጠር ለሚገኘው ገበሬ እና የጤና ባለሙያ ቀጥተኛ የተግባር መሣሪያ (Actionable Tool) ካላደረግነው፣ የሚከሰቱ ተፍጥሮኣዊ አደጋዎችን ወደ ከፍተኛ ቀውስ መለወጣቸው አይቀሬ ነው።” ሲሉ የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲቲውት ጄኔራል ዳይሬክተር ዶ/ር ፈጠነ ተሾመ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፦ በክፍል አንድ፦ የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃዎችን ከቅድመ-ማስጠንቀቂያ ወደ ቀደምት እርምጃ በመቀየር የድርቅ፣ የጎርፍ፣ የወባ እና የኮሌራ አደጋዎችን በመረጃ  መመከት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ፤ በክፍል ሁለት፦ የማህበራዊ ሚዲያ ዕድሎችንና መርዛማ ተፅዕኖዎችን፣ የጋቦን ከ16 ዓመት በታች ህፃናት እገዳ ተሞክሮን እንዲሁም ታዳጊዎችን ከሳይበር ትንኮሳና ከኦንላይን ብዝበዛ የመጠበቅ አህጉራዊ አቅጣጫዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ወጣቶች መካከል አንዱ ከሆነው ብሩክ ጫላ ጋር በጥልቀት እንዳስሰዋለን፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

9/30/26 • 120:08

“የBRICS+ መስፋፋት የመጠን መጨመር ብቻ ሳይሆን የዓለም የጂኦ-ፖለቲካ እና የጂኦ-ኢኮኖሚ የኃይል ሚዛን ከምዕራባውያን የበላይነት ወደ ባለብዙ ዋልታ/Multipolar/ ሥርዓት እየተቀየረ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው። ለአፍሪካ ሀገራትም ምዕራባውያን ያዘጋጁትን የፖሊሲ አማራጭ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ አጋሮችን የመምረጥ አቅም (Strategic Leverage) ይሰጣቸዋል።” ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናት እና ምርምር ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር አበራ ኤሊያስ ተናግረዋል።በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ (African Heights) ዝግጅታችን፦•    BRICS+ እና የአዲሱ ዓለም ሥርዓት እውነታ፦ BRICS+ ከዓለም ህዝብ ቁጥር 45% በላይ እና ከነዳጅ ምርት 40% በላይ በመወከል በዓለም ኢኮኖሚ ላይ እያመጣ ያለውን መዋቅራዊ ለውጥ፤•    የNDB የተግባር እርምጃዎች፦ አዲሱ የልማት ባንክ (NDB) ያለ ፖለቲካዊ ቅድመ-ሁኔታ የሚያቀርበውን ፋይናንስ፣ በሀገር ውስጥ ምንዛሬ ብድር የመስጠት እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት የማድረጉን ጥቅም፤•    የኢትዮጵያ ቦታ እና የጂኦ-ኢኮኖሚ ተፅዕኖ፦ ኢትዮጵያ በBRICS+ ውስጥ ያላትን የዲፕሎማሲ አቅም (Diplomatic Leverage)፣ የህዳሴ ግድብ የኃይል ማከፋፈያ መስመሮችና የዲጂታል ኢኮኖሚን በNDB ፋይናንስ የመገንባት ዕድሎች፤ እንዲሁም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከዶ/ር አበራ ኤሊያስ ጋር በስፋትና በጥልቀት ተመልክተነዋል።

9/30/26 • 120:08